ዘዳግም 3:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን እጅግ ከብቶች እንዳሉአችሁ አውቃለሁና ሴቶቻችሁና ልጆቻችሁ፥ ከብቶቻችሁም በሰጠኋችሁ ከተሞች ይቀመጣሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሆኖም ሚስቶቻችሁና ልጆቻችሁ፣ (ብዙ ከብቶች እንዳሏችሁም ስለማውቅ) ከብቶቻችሁም በሰጠኋችሁ ከተሞች ውስጥ ይቈዩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን፥ ብዙ ከብቶች እንዳሏችሁ አውቃለሁና፥ ሚስቶቻችሁ፥ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ በሰጠኋችሁ ከተሞች ይቀራሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዙ ከብት እንዳላችሁ ዐውቃለሁ፤ ስለዚህም እዚህ መቅረት የሚችሉት ሚስቶቻችሁ፥ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ ብቻ ናቸው፤ ስለዚህም እነርሱን እኔ በሰጠኋችሁ ከተሞች ወደ ኋላ ትታችሁ ትሄዳላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እጅግ ከብቶች እንዳሉአችሁ አውቃለሁና ሴቶቻችሁና ልጆቻችሁ ከብቶቻችሁም በሰጠኋችሁ ከተሞች ይቀመጣሉ፤ |
ሚስቶቻችሁና ልጆቻችሁ ከብቶቻችሁም ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ በሰጣችሁ በዚች ምድር ይቀመጡ፤ እናንተ፥ ጽኑዓን ሁሉ ግን ታጥቃችሁ በወንድሞቻችሁ ፊት ዮርዳኖስን ተሻገሩ፤ ለእነርሱም ተዋጉላቸው።