ለእነርሱም፥ ከእነርሱም በኋላ ለልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ ለዘለዓለም እንዲፈሩኝ ሌላ መንገድና ሌላ ልብ እሰጣቸዋለሁ።
ዘዳግም 29:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ዛሬ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ከእኛ ጋር በዚህ ከሚቆም ሰው ጋር፥ ዛሬም ከእኛ ጋር በዚህ ከሌለ ሰው ጋር ነው እንጂ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐብራችሁን በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት እዚህ ከቆማችሁት ጋራ ብቻ ሳይሆን፣ ዛሬ እዚህ ከሌሉትም ጋራ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ዛሬ በአምላካችን በጌታ ፊት ከእኛ ጋር በዚህ ከሚቆም ሰው ጋር እንዲሁም ዛሬም ከእኛ ጋር በዚህ ከሌለ ሰው ጋር ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ይህን ቃል ኪዳን የሚገባው ዛሬ በዚህ ስፍራ በፊቱ ከቆምነው ከእኛ ሁሉና ዛሬም ከእኛ ጋር እዚህ ከሌሉት ጋር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ዛሬ በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት ከእኛ ጋር በዚህ ከሚቆም ሰው ጋር፥ ዛሬም ከእኛ ጋር በዚህ ከሌለ ሰው ጋር ነው እንጂ፤ |
ለእነርሱም፥ ከእነርሱም በኋላ ለልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ ለዘለዓለም እንዲፈሩኝ ሌላ መንገድና ሌላ ልብ እሰጣቸዋለሁ።
ወደ ጽዮን የሚሄዱበትን ጎዳና ይመረምራሉ፤ ፊታቸውንም ወደ ሀገራቸው ይመልሳሉ፤ የዘለዓለም ቃልኪዳን አይረሳምና መጥተው ወደ ፈጣሪያቸው ወደ እግዚአብሔር ይማጠናሉ።
የማያምን ባል በሚስቱ ይቀደሳልና፤ የማታምን ሚስትም በባልዋ ትቀደሳለችና፤ ያለዚያማ ልጆቻቸው ርኩሳን ይሆናሉ፤ አሁን ግን ቅዱሳን ናቸው።
ነገር ግን እኛ በግብፅ ምድር እንደ ተቀመጥን በመካከላቸውም ባለፋችሁባቸው አሕዛብ መካከል እንዳለፍን ዐውቃችኋልና፥
እግዚአብሔር ዛሬ በዚህ በሕይወት ካላችሁት ከእናንተ ከሁላችሁ ጋር እንጂ ከአባቶቻችሁ ጋር ይህችን ቃል ኪዳን አላጸናም።