ዘዳግም 28:61 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም ይህ ሕግ ባለበት መጽሐፍ ውስጥ ያልተጻፈውን ደዌ ሁሉ፥ መቅሠፍትንም ሁሉ እስክትጠፋ ድረስ እግዚአብሔር ያመጣብሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም እግዚአብሔር በዚህ የሕግ መጽሐፍ ያልተጻፈውን ማንኛውንም ዐይነት ደዌና መከራ እስክትጠፋ ድረስ ያመጣብሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተጨማሪም ጌታ በዚህ የሕግ መጽሐፍ ያልተጻፈውን ማንኛውንም በሽታና መከራ እስክትጠፋ ድረስ ያመጣብሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ሕግ በተጻፉበት በዚህ መጽሐፍ ያልተጠቀሱ በሽታዎችንና መቅሠፍቶችን ሁሉ እስክትጠፋ ድረስ ይልክብሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም ይህ ሕግ ባለበት መጽሐፍ ውስጥ ያልተጻፈውን ደዌ ሁሉ መቅሠፍትም ሁሉ እስክትጠፋ ድረስ እግዚአብሔር ያመጣብሃል። |
እግዚአብሔርም በዚህ ሕግ መጽሐፍ እንደ ተጻፈው እንደ ቃል ኪዳኑ ርግማን ሁሉ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ለጥፋት ይለየዋል።