ዘዳግም 28:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወይራ ዛፍ በሀገርህ ሁሉ ይሆንልሃል፤ ፍሬውም ይረግፋልና ዘይቱን አትቀባም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአገርህ ምድር ሁሉ የወይራ ዛፍ ይኖርሃል፤ ፍሬው ስለሚረግፍብህ ግን፣ ዘይቱን አትጠቀምበትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወይራ ዛፍ በምድርህ ሁሉ ይኖርሃል፤ ፍሬው ስለሚረግፍብህ ግን ዘይቱን አትቀባም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወይራ ዛፍ በምድርህ በየስፍራው ይበቅላል፤ ነገር ግን የወይራው ፍሬ ያለ ጊዜው ስለሚረግፍ የወይራ ዘይት አይኖርህም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወይራ ዛፍ በአገርህ ሁሉ ይሆንልሃል፤ ወይራህም ይረግፋልና ዘይቱን አትቀባም። |
እግዚአብሔር ስምሽን፦ በመልካም ፍሬ የተዋበችና የለመለመች የወይራ ዛፍ ብሎ ጠራው፤ ከመቈረጥዋም ድምፅ የተነሣ በላይዋ እሳት ነደደባት፤ ቅርንጫፎችዋም ተሰብረዋል።
ትዘራለህ፥ ነገር ግን አታጭድም፥ ወይራውንም ትጨምቃለህ፥ ነገር ግን ዘይቱን አትቀባም፥ ወይኑንም ትጨምቃለህ፥ ነገር ግን የወይን ጠጁን አትጠጣም።