ዘዳግም 28:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይን ትተክላለህ፤ ታበጀውማለህ፤ ከወይኑም አትጠጣም፤ ክፉ ትልም ይበላዋልና በእርሱ ደስ አይልህም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይን ትተክላለህ፤ ትንከባከበዋለህ፤ ነገር ግን ትል ይበላዋልና ዘለላውን አትሰበስብም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይን ተክለህ ትንከባከበዋለህ፤ ነገር ግን ትል ስለሚበላው ዘለላውን አትሰበስብም ወይም ከወይኑ አትጠጣም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወይኑን ሐረግ ትል ስለሚበላው ወይን ተክለህ ትንከባከበዋለህ፤ ነገር ግን የወይን ዘለላ ሰብስበህ አትበላም፤ ወይም ከእርሱ የወይን ጠጅ አትጠጣም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይን ትተክላለህ ታበጀውማለህ፤ ትልም ይበላዋልና ከእርሱ ምንም አትሰበስብም፥ የወይን ጠጁንም አትጠጣም። |
ዐሥር ጥማድ በሬ ካረሰው የወይን ቦታ አንድ ፊቀን ወይን ጠጅ ይወጣል፤ ስድስት መስፈሪያ የዘራ ሦስት መሥፈሪያ ብቻ ያገባል።
ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥