በዚያም ዘመን ለሚወጣውና ለሚገባው ሰላም አይሆንለትም፤ በሀገሮችም በሚኖሩት ሁሉ ላይ ታላቅ የእግዚአብሔር ቍጣ ይሆናል።
ዘዳግም 28:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ በመግባትህና በመውጣትህም ርጉም ትሆናለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስትገባ ትረገማለህ፤ ስትወጣም ትረገማለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ስትገባ ትረገማለህ፤ ስትወጣም ትረገማለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስትገባና ስትወጣ የተረገምህ ትሆናለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ በመግባትህ ርጉም ትሆናለህ፥ በመውጣትህም ርጉም ትሆናለህ። |
በዚያም ዘመን ለሚወጣውና ለሚገባው ሰላም አይሆንለትም፤ በሀገሮችም በሚኖሩት ሁሉ ላይ ታላቅ የእግዚአብሔር ቍጣ ይሆናል።
እኔን ስለተውኸኝ፥ ስለ ሥራህ ክፋት፥ እስክትጠፋ፥ ፈጥነህም እስክታልቅ ድረስ በምትሠራው ሥራ ሁሉ እግዚአብሔር ችግርን፥ ረኃብን፦ ቸነፈርንም ይልክብሃል።