ዘዳግም 27:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮርዳኖስንም በተሻገራችሁ ጊዜ፥ ዛሬ እንዳዘዝኋችሁ፥ እነዚህን ድንጋዮች በጌባል ተራራ አቁሙ፤ በኖራም ምረጓቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮርዳኖስን እንደ ተሻገርህም፣ ዛሬ ባዘዝሁህ መሠረት እነዚህን ድንጋዮች በጌባል ተራራ ላይ ትከላቸው፤ በኖራም ቅባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮርዳኖስን እንደ ተሻገርህም፥ ዛሬ ባዘዝሁህ መሠረት እነዚህን ድንጋዮች በጌባል ተራራ ላይ ትከላቸው፤ በኖራም ምረጋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮርዳኖስን በተሻገርህ ጊዜ እኔ ዛሬ ባዘዝኩህ መሠረት እነዚህን ድንጋዮች በዔባል ተራራ ላይ አቁመህ በኖራ ለስናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮርዳኖስንም በተሻገርህ ጊዜ፥ ዛሬ እንዳዘዝሁህ፥ እነዚህን ድንጋዮች በጌባል ተራራ አቁም፥ በኖራም ምረጋቸው። |
አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ ታላላቅ ድንጋዮችን ለእናንተ አቁሙ፤ በኖራም ምረጓቸው።