Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 27:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር ዮር​ዳ​ኖ​ስን በተ​ሻ​ገ​ራ​ችሁ ጊዜ ታላ​ላቅ ድን​ጋ​ዮ​ችን ለእ​ና​ንተ አቁሙ፤ በኖ​ራም ምረ​ጓ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ፣ ጥቂት ትልልቅ ድንጋዮችን አቁምና በኖራ ቅባቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ጌታ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ፥ ጥቂት ትልልቅ ድንጋዮችን አቁምና በኖራም ምረጋቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግራችሁ አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በምትገባበት ጊዜ ታላላቅ የሆኑ ጥቂት ድንጋዮችን አቁመህ በኖራ ለስነው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር ዮርዳኖስን በተሻገርህ ጊዜ ታላላቅ ድንጋዮችን ለአንተ አቁም፥ በኖራም ምረጋቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 27:2
16 Referencias Cruzadas  

ማን በብ​ረት ብር​ዕና በእ​ር​ሳስ፥ በዓ​ለት ላይ በቀ​ረ​ፀው!


ሌላ ልብ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በው​ስ​ጣ​ቸ​ውም አዲስ መን​ፈስ አሳ​ድ​ራ​ለሁ፤ ከሥ​ጋ​ቸ​ውም ውስጥ የድ​ን​ጋ​ዩን ልብ አወ​ጣ​ለሁ፤ የሥ​ጋ​ንም ልብ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤


አዲስ ልብ​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ አዲስ መን​ፈ​ስ​ንም በው​ስ​ጣ​ችሁ አኖ​ራ​ለሁ፤ የድ​ን​ጋ​ዩ​ንም ልብ ከሥ​ጋ​ችሁ አወ​ጣ​ለሁ፤ የሥ​ጋ​ንም ልብ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ።


አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዕ​ጣ​ችሁ ለሁ​ል​ጊዜ የሚ​ሰ​ጣ​ች​ሁን ምድር ትገ​ቡና ትወ​ርሱ ዘንድ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ራ​ላ​ችሁ፤ ትወ​ር​ሱ​አ​ታ​ላ​ች​ሁም፤ ትቀ​መ​ጡ​ባ​ታ​ላ​ች​ሁም።


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ ወደ​ሚ​ሰ​ጥህ ምድር በገ​ባህ ጊዜ፥ በወ​ረ​ስ​ሃ​ትም፥ በኖ​ር​ህ​ባ​ትም ጊዜ፥


ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “ዛሬ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁን ትእ​ዛዝ ታደ​ርጉ ዘንድ ዕወቁ፤


የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ራ​ችሁ፥ ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስስ ምድር፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር ትገቡ ዘንድ በተ​ሻ​ገ​ራ​ችሁ ጊዜ፥ የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ሁሉ በድ​ን​ጋ​ዮች ላይ ጻፉ።


ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም በተ​ሻ​ገ​ራ​ችሁ ጊዜ፥ ዛሬ እን​ዳ​ዘ​ዝ​ኋ​ችሁ፥ እነ​ዚ​ህን ድን​ጋ​ዮች በጌ​ባል ተራራ አቁሙ፤ በኖ​ራም ምረ​ጓ​ቸው።


“ልት​ወ​ር​ሱ​አት በም​ት​ገ​ቡ​ባት ምድር ታደ​ር​ጉት ዘንድ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ስ​ተ​ም​ራ​ችሁ ያዘ​ዘው ትእ​ዛ​ዝና ሥር​ዐት፥ ፍር​ድም ይህ ነው።


“እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማ፤ ከአ​ንተ የበ​ለ​ጡ​ት​ንና የበ​ረ​ቱ​ትን አሕ​ዛብ፥ የቅ​ጽ​ራ​ቸው ግንብ እስከ ሰማይ የሚ​ደ​ርስ ታላ​ላ​ቆች ከተ​ሞ​ችን ለመ​ው​ረስ ትገቡ ዘንድ ዛሬ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ረ​ዋ​ለህ።


“በሰ​ፈሩ መካ​ከል ዕለፉ፥ ሕዝ​ቡ​ንም፦ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር እስከ ሦስት ቀን ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ራ​ችሁ ልት​ወ​ር​ሱ​አት ትገ​ቡ​ባ​ታ​ላ​ች​ሁና ስን​ቃ​ች​ሁን አዘ​ጋጁ ብላ​ችሁ እዘ​ዙ​አ​ቸው።”


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሕዝቡ ሁሉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ፈጽ​መው በተ​ሻ​ገሩ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


የዚያ ጊዜም ኢያሱ በጌ​ባል ተራራ ላይ ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊ​ያን ሠራ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዳ​ዘዘ፥ በሙ​ሴም ሕግ መጽ​ሐፍ እንደ ተጻ​ፈው፥ መሠ​ዊ​ያው ካል​ተ​ወ​ቀ​ረና ብረት ካል​ነ​ካው ድን​ጋይ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ላይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ፤ የደ​ኅ​ን​ነ​ት​ንም መሥ​ዋ​ዕት ሠዋ።


ኢያ​ሱም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ፊት በድ​ን​ጋ​ዮቹ ላይ ሙሴ የጻ​ፈ​ውን ይህን ሁለ​ተ​ኛ​ውን ሕግ በድ​ን​ጋ​ዮች ላይ ጻፈ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos