የሴትንና የሴት ልጅዋን ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የወንድ ልጅዋን ሴት ልጅ ወይም የሴት ልጅዋን ሴት ልጅ ኀፍረተ ሥጋዋን ትገልጥ ዘንድ አታግባ፤ ዘመዶች ናቸው፤ ኀጢአት ነውና።
ዘዳግም 27:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከአማቱ ጋር የሚተኛ ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ። ከዋርሳው ጋር የሚተኛ ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይሁን ይላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከዐማቱ ጋራ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “‘ከዐማቱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ ‘ከዐማቱ ጋር ግንኙነት የሚፈጽም ወንድ ሁሉ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይበሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአማቱ ጋር የሚተኛ ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ። |
የሴትንና የሴት ልጅዋን ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የወንድ ልጅዋን ሴት ልጅ ወይም የሴት ልጅዋን ሴት ልጅ ኀፍረተ ሥጋዋን ትገልጥ ዘንድ አታግባ፤ ዘመዶች ናቸው፤ ኀጢአት ነውና።
ማናቸውም ሰው እናቲቱንና ልጂቱን ቢያገባ ኀጢአት ነው፤ በመካከላቸው ኀጢአት እንዳይሆን እርሱንና እነርሱን በእሳት ያቃጥሉአቸው።