La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 25:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በደ​ለ​ኛ​ውም መገ​ረፍ ቢገ​ባው እን​ዲ​ገ​ረፍ ፈራጁ በፊቱ በም​ድር ላይ ያጋ​ድ​መው፤ የግ​ር​ፋ​ቱም ቍጥር እንደ ኀጢ​አቱ መጠን ይሁን።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በደለኛው ሰው መገረፍ የሚገባው ሆኖ ከተገኘ፣ ዳኛው መሬት ላይ ያጋድመው፤ ለጥፋቱ ተመጣጣኝ የሆነ ግርፋት እርሱ ባለበት ይገረፍ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በደለኛው ሰው መገረፍ የሚገባው ሆኖ ከተገኘ ዳኛው መሬት ላይ ያጋድመው፤ ለጥፋቱ ተመጣጣኝ የሆነ ግርፋት እርሱ ባለበት ይገረፍ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በደል የፈጸመው ሰው በግርፋት እንዲቀጣ ቢያስፈልግ፥ በደረቱ መሬት ላይ አስተኝተው ጀርባውን እንዲገርፉት ዳኛው ይዘዝ፤ የሚገረፈውም ዳኛው ባለበትና የግርፋቱም ቊጥር የሚወሰነው ወንጀለኛው በሠራው በደል መጠን ይሆናል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በደለኛውም መገረፍ ቢገባው እንዲገረፍ ፈራጁ በፊቱ በምድር ላይ ያጋድመው፤ የግርፋቱም ቁጥር እንደ ኃጢአቱ መጠን ይሁን።

Ver Capítulo



ዘዳግም 25:2
10 Referencias Cruzadas  

እነ​ር​ሱ​ንም ተቈ​ጣ​ኋ​ቸው፤ ረገ​ም​ኋ​ቸ​ውም፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ዐያ​ሌ​ዎ​ቹን መታሁ፤ ጠጕ​ራ​ቸ​ው​ንም ነጨሁ፤ እን​ዲ​ህም ብዬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አማ​ል​ኋ​ቸው፥ “ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸው አት​ስጡ፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ችሁ አት​ው​ሰዱ።


ለክፉዎች ሰዎች መቅሠፍት ተዘጋጅቶላቸዋል፥ ለሰነፎችም እንደዚሁ ቅጣት።


ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ፤


በዚያን ጊዜ በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን ገርፎ ሊሰቀል አሳልፎ ሰጠ።


ጳው​ሎ​ስም መልሶ፥ “አንተ የተ​ለ​ሰነ ግድ​ግዳ በሕግ ልት​ፈ​ር​ድ​ብኝ ተቀ​ም​ጠህ ሳለ ያለ ሕግ እመታ ዘንድ ታዝ​ዛ​ለ​ህን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ታ​ሃል” አለው።


እሺም አሰ​ኛ​ቸው፤ ሐዋ​ር​ያ​ት​ንም ጠር​ተው ገረ​ፉ​አ​ቸው፤ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም በኢ​የ​ሱስ ስም እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ገሥ​ጸው ተዉ​አ​ቸው።


ኀጢአት አድርጋችሁ ስትጎሰሙ ብትታገሡ፥ ምን ክብር አለበት? ነገር ግን መልካም አድርጋችሁ መከራን ስትቀበሉ ብትታገሡ፥ ይህ ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋና ይገባዋል።


ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።