ዘዳግም 24:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከወንድሞችህ ወይም በሀገርህ ውስጥ ከአሉት መጻተኞች ድሃና ችግረኛ የሆነውን ምንደኛ ደመወዙን አትከልክለው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ችግረኛና ድኻ የሆነውን የምንዳ ሠራተኛ እስራኤላዊ ወንድምህም ሆነ፣ ከከተሞችህ በአንዲቱ የሚኖረውን መጻተኛ አትበዝብዘው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ድኻና ችግረኛ የሆነውን የምንዳ ሠራተኛ እስራኤላዊ ወንድምህም ሆነ፥ ከከተሞችህ በአንዲቱ የሚኖረውን መጻተኛ አትበዝብዘው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስራኤላዊውም ሆነ ወይም ከአገርህ ከተማዎች በአንዱ የሚኖር የውጪ አገር ተወላጅ ድኻና ችግረኛ ሆኖ የተቀጠረውን ማናቸውንም ሰው አትበዝብዘው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድሀና ችግረኛ የሆነውን ምንደኛ፥ ከወንድሞችህ ወይም በምድርህ በአገርህ ደጅ ውስጥ ከሚቀመጡት መጻተኞች ቢሆን፥ አታስጨንቀው። |
በአንቺ ውስጥ አባትንና እናትን አቃለሉ፤ በመካከልሽ በመጻተኛው ላይ በደልን አደረጉ፤ በአንቺ ውስጥ ድሀ አደጉንና መበለቲቱን አስጨነቁ።
የድሆችን ራስ ይቀጠቅጣሉ፤ የትሑታንንም ፍርድ ያጣምማሉ፤ የአምላካቸውንም ስም ያረክሱ ዘንድ አባትና ልጁ ወደ አንዲት ሴት ይገባሉ፤
በሰማርያ ተራራ የምትኖሩ፥ ድሆችንም የምትበድሉ፥ ችግረኞችንም የምታስጨንቁ፥ ጌቶቻቸውንም፦ አምጡ እንጠጣ የምትሉ እናንተ የባሳን ላሞች ሆይ! ይህን ቃል ስሙ።
ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፣ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
“አምላክህ እግዚአብሔር በሰጠህ ምድር ካሉ ከተሞች በአንዲትዋ ውስጥ ከሚኖሩ ከወንድሞችህ አንዱ ቢቸገር ልብህን አታጽና፤ ለወንድምህ ከመስጠት እጅህን አትመልስ።