ወደ እግዚአብሔርም የተጠጋ መጻተኛ፥ “በእውነት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ይለየኛል” አይበል፤ ጃንደረባም፥ “እነሆ፥ እኔ እንደ ደረቀ ዛፍ ነኝ” አይበል።
ዘዳግም 23:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዲቃላ ወደ እግዚአብሔር ቤት አይግባ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዲቃላም ይሁን የዲቃላው ዘር የሆነ ሁሉ፣ እስከ ዐሥር ትውልድ ድረስ እንኳን ቢሆን ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከጋብቻ ውጪ የተወለደ ወደ ጌታ ጉባኤ አይግባ፤ እስከ ዐሥር ትውልድ ድረስ እንኳን ቢሆን ወደ ጌታ ጉባኤ አይግባ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከጋብቻ ውጪ ዲቃላ ሆኖ የተወለደና የእርሱም ዘር ሆኖ የተወለደ ሁሉ እስከ ዐሥር ትውልድ እንኳ ወደ እግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ ገብቶ አይቈጠር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዲቃላ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ፤ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። |
ወደ እግዚአብሔርም የተጠጋ መጻተኛ፥ “በእውነት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ይለየኛል” አይበል፤ ጃንደረባም፥ “እነሆ፥ እኔ እንደ ደረቀ ዛፍ ነኝ” አይበል።
ወይም ጎባጣ፥ ወይም ድንክ፥ ወይም ዐይነ መጭማጫ፥ ወይም ቅንድበ መላጣ፥ ወይም እከካም፥ ወይም ቋቍቻም፥ ወይም የአባለዘሩ ፍሬ አንድ የሆነ ነውረኛ ሁሉ አይቅረብ።
እናንተ ግን የአባታችሁን ሥራ ትሠራላችሁ።” እነርሱም፥ “እኛ ከዝሙት አልተወለድንም፤ ነገር ግን አንድ አባት አለን፤ እርሱም እግዚአብሔር ነው” አሉት።
“አሞናዊ ወይም ሞዓባዊ ወደ እግዚአብሔር ቤት አይግባ፤ እስከ ዐሥር ትውልድ ድረስ ለዘለዓለም ወደ እግዚአብሔር ቤት አይግባ።