“ሥርዐቴን ጠብቁ፤ በበሬህ በባዕድ ቀንበር አትረስ፤ በወይን ቦታህ የተለያየ ዘር አትዝራ፤ ከሁለት ዐይነት ነገር የተሠራ ልብስ ኀፍረት ነውና አትልበስ።
ዘዳግም 22:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ፍሬውንና የዘራኸውን ዘር ከወይንህ ፍሬ ጋር እንዳትለቅም በወይንህ ቦታ ላይ የተለያየ ዓይነት ተክል አትትከል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በወይን ተክል ቦታህ ውስጥ ሁለት ዐይነት ዘር አትዝራ፤ ይህን ካደረግህ፣ የዘራኸው ሰብል ብቻ ሳይሆን፣ የወይን ፍሬህም ይጠፋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የዘራኸው ዘርና ከወይኑ የወጣው አንድ ሆነው እንዳይጠፉብህ በወይንህ ቦታ ላይ ሁለት ዓይነት ዘር አትዝራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በወይን ተክልህ ውስጥ ሌላ ዘር አትዝራ፤ ይህን ብታደርግ በወይኑ ፍሬም ሆነ በሌላው ሰብል መጠቀም አትችልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዘራኸው ዘርና ከወይኑ የወጣው አንድ ሆነው እንዳይጠፉብህ በወይንህ ቦታ ላይ ሁለት ዓይነት ዘር አትዝራ። |
“ሥርዐቴን ጠብቁ፤ በበሬህ በባዕድ ቀንበር አትረስ፤ በወይን ቦታህ የተለያየ ዘር አትዝራ፤ ከሁለት ዐይነት ነገር የተሠራ ልብስ ኀፍረት ነውና አትልበስ።
“ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።
በእግዚአብሔር ቸርነትና ይቅርታ መመኪያችንና የነፃነታችን ምስክር ይህቺ ናትና፥ በሥጋዊ ጥበብ ሳይሆን፥ በእግዚአብሔር ጸጋ በዚህ ዓለም፥ ይልቁንም በእናንተ ዘንድ ተመላለስን።
ነገር ግን እባብ ሔዋንን በተንኰሉ እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ከክርስቶስ የዋህነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ።