ንጉሡም አለው፥ “ሂድና እንደ ነገረህ አድርግ፤ ገድለህም ቅበረው፤ ኢዮአብም በከንቱ ያፈሰሰውን ደም ከእኔና ከአባቴ ቤት ታርቃለህ።
ዘዳግም 21:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተም በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ጥሩ የሆነውን ባደረግህ ጊዜ የንጹሑን ደም በደል ከመካከላቸው ታርቃለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተም በእግዚአብሔር ፊት ቀና የሆነውን ስታደርግ፣ የንጹሑን ደም የማፍሰስ በደልን ከመካከልህ ታስወግዳለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተም በጌታ ፊት ቀና የሆነውን ስታደርግ፥ የንጹሑን ደም የማፍሰስ በደልን ከመካከልህ ታስወግዳለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛውን ነገር ስለምታደርግ ስለ ንጹሑ ሰው ግድያ ወንጀል ተጠያቂ አትሆንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም በእግዚአብሔር ዓይን የቀናውን ባደረግህ ጊዜ የንጹሑን ደም በደል ከመካከልህ ታርቃለህ። |
ንጉሡም አለው፥ “ሂድና እንደ ነገረህ አድርግ፤ ገድለህም ቅበረው፤ ኢዮአብም በከንቱ ያፈሰሰውን ደም ከእኔና ከአባቴ ቤት ታርቃለህ።
በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ጥሩ የሆነውን ነገር ስታደርግ ለአንተ፥ ከአንተም በኋላ ለልጆችህ መልካም እንዲሆንላችሁ፥ አትብላው።
ዛሬም እኔ የማዝዝህን ትእዛዝ ሁሉ ብትጠብቅ፥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ጥሩ የሆነውን ብታደርግ፥ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ ለእርሱ ልጅ ትሆናለህ።