ዘዳግም 21:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለልጆቹ ከብቱን በሚያወርስበት ቀን ከተጠላችው ሚስት በተወለደው በበኵሩ ፊት ከተወደደችው ሚስት የተወለደውን ልጅ በኵር ያደርገው ዘንድ አይገባውም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንብረቱን ለልጆቹ በሚያወርስበት ጊዜ፣ የብኵርናን መብት ከማይወድዳት ሚስቱ ከወለደው በኵር ልጅ ገፎ፣ ከሚወድዳት ሚስቱ ለተወለደው ልጁ በአድልዎ መስጠት አይገባውም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንብረቱን ለልጆቹ በሚያወርስበት ጊዜ፥ የብኩርናን መብት ከማይወዳት ሚስቱ ከወለደው በኩር ልጅ ገፎ፥ ከሚወዳት ሚስቱ ለተወለደው ልጁ፥ በአድልዎ መስጠት አይገባውም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ ያ ሰው ሀብቱንና ንብረቱን ለልጆቹ በሚያካፍልበት ጊዜ ለበኲር ልጁ ሊሰጥ የሚገባውን ድርሻ በተለይ ከሚያፈቅራት ሚስቱ ለተወለደው ልጁ በመስጠት አድልዎ ማድረግ አይገባውም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለልጆቹ ከብቱን በሚያወርስበት ቀን ከተጠላችው ሚስት በተወለደው በበኩሩ ፊት ከተወደደችው ሚስት የተወለደውን ልጅ በኩር ያደርገው ዘንድ አይገባውም፤ |
ከሜራሪም ልጆች ለነበረው ለሖሳ ፊተኛውን በር የሚጠብቁ ልጆች ነበሩት፤ አለቃውም ሰምሪ ነበረ፤ በኵር አልነበረም፤ አባቱ ግን አለቃ አደረገው፤
አባታቸውም ብዙ ስጦታ፥ ብርና ወርቅ፥ የከበረም ዕቃ፥ በይሁዳም የተመሸጉትን ከተሞች ሰጣቸው፤ መንግሥቱን ግን የበኵር ልጁ ስለሆነ ለኢዮራም ሰጠው።
ልጁ በብዙዎች ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ አስቀድሞ ያወቃቸውንና የመረጣቸውን እነርሱን ልጁን ይመስሉ ዘንድ አዘጋጅቶአቸዋል።
“ለአንድ ሰው አንዲቱ የተወደደች፥ አንዲቱም የተጠላች ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት፥ ለእርሱም የተወደደችው፥ ደግሞም የተጠላችው ልጆችን ቢወልዱ፥ በኵሩም ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ ቢሆን፥
ነገር ግን ከከብቱ ሁለት እጥፍ ለእርሱ በመስጠት ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ በኵር እንደ ሆነ ያስታውቅ። የኀይሉ መጀመሪያ ነውና በኵርነቱ የእርሱ ነው።
አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ፥ እውነትን ሁሉ፥ ቅንነትንም ሁሉ፥ ጽድቅንም ሁሉ፥ ንጽሕናንም ሁሉ፥ ፍቅርንና ስምምነትንም ሁሉ፥ በጎነትም ቢሆን፥ ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን ሁሉ አስቡ።