በአብራምና በሎጥ መንጎች ጠባቆች መካከልም ጠብ ሆነ፤ በዚያ ዘመን ከነዓናውያንና ፌርዛውያን በዚያች ምድር ተቀምጠው ነበር።
ዘዳግም 20:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር እንዳዘዘህ ኬጤዎናዊዉን፥ አሞሬዎናዊዉን፥ ከነዓናዊዉንም፥ ፌርዜዎናዊዉንም፥ ኤዌዎናዊዉንም፥ ኢያቡሴዎናዊዉንም፥ ጌርጌሴዎናዊዉንም ፈጽመህ ትረግማቸዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኬጢያዊውን፣ አሞራዊውን፣ ከነዓናዊውን፣ ፌርዛዊውን፣ ኤዊያዊውንና ኢያቡሳዊውን አምላክህ እግዚአብሔር ባዘዘህ መሠረት ፈጽመህ ደምስሳቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኬጠያዊውን፥ አሞራዊውን፥ ከነዓናዊውን፥ ፌርዛዊውን፥ ኤዊያዊውን፥ ኢያቡሳዊውን አምላክህ ጌታ ባዘዘህ መሠረት ፈጽመህ ደምስሳቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም በሒታውያን፥ በአሞራውያን፥ በከነዓናውያን፥ በፈሪዛውያን፥ በሒዋውያንና በኢያቡሳውያን ላይ እግዚአብሔር ባዘዛችሁ መሠረት ሕዝቡን በሙሉ ደምስሱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ለአማልክቶቻቸው ያደረጉትን ርኩሰት ሁሉ ታደርጉ ዘንድ እንዳያስተምሩአችሁ፥ በአምላካችሁም በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት እንዳትሠሩ፥ አምላክህ እግዚአብሔር እንዳዘዘህ ኬጢያዊውን አሞራዊውንም ከነዓናዊውንም ፌርዛዊውንም ኤዊያዊውንም ኢያቡሳዊውንም ፈጽመህ ታጠፋቸዋለህ። |
በአብራምና በሎጥ መንጎች ጠባቆች መካከልም ጠብ ሆነ፤ በዚያ ዘመን ከነዓናውያንና ፌርዛውያን በዚያች ምድር ተቀምጠው ነበር።
ደግሞም በዚያ የዔናቅን ዘሮች አየን፤ በአዜብ በኩል ዐማሌቅ ተቀምጦአል፤ በተራሮችዋም ኬጤዎናዊውና ኤዌዎናዊውም፥ ኢያቡሴዎናዊው፥ አሞሬዎናዊውም ተቀምጠዋል፤ ከነዓናዊውም በባሕር ዳርና በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ተቀምጦአል።”
ለአማልክቶቻቸው ያደረጉትን ርኵሰት ሁሉ ታደርጉ ዘንድ እንዳያስተምሩአችሁ፥ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት እንዳትሠሩ ትረግማቸዋለህ።
ከተማዪቱም በእርስዋም ያለው ሁሉ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር እርም ይሆናሉ፤ የላክናቸውን መልእክተኞች ስለ ሸሸገች ዘማዊቱ ረዓብ፥ ከእርስዋም ጋር በቤቷ ውስጥ ያሉ ሁሉ ብቻ በሕይወት ይኖራሉ።