በዚያችም ሌሊት ተነሣ፥ ሁለቱን ሚስቶቹንና ሁለቱን ዕቁባቶቹን ዐሥራ አንዱንም ልጆቹን ይዞ የያቦቅን ወንዝ ተሻገረ።
ዘዳግም 2:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳሩ ግን አምላካችን እግዚአብሔር እንዳዘዘን ወደ አሞን ልጆች ምድር፥ በያቦቅም ወንዝ አጠገብ ወደ አለው ስፍራ ሁሉ፥ በተራራማውም ሀገር ወደ አሉ ከተሞች አልደረስንም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ አምላካችን እግዚአብሔር በሰጠው ትእዛዝ መሠረት፣ ወደ ማንኛውም የአሞናውያን ምድር ወይም በያቦቅ ወንዝ መውረጃ ወዳለው ምድር ወይም ደግሞ በኰረብቶች ወዳሉት ከተሞች ዙሪያ ዐልፋችሁ አልሄዳችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብቻ ጌታ አምላካችን ወደ ከለከለን፥ ወደ አሞን ልጆች ምድር በያቦቅም ወንዝ አጠገብ ወዳለው ስፍራ ሁሉ በተራራማውም አገር ወዳሉት ከተሞች አልቀረብንም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ወደ ዐሞናውያን ግዛት አጠገብ ወይም ወደ ያቦቅ ወንዝ ዳርቻ ወይም ወደ ኮረብታማይቱ አገር ከተሞች ወይም እግዚአብሔር እንዳንደርስባቸው ወዳዘዘን እነዚህን ከመሳሰሉት አገሮች ወደ አንዲቱ እንኳ አልቀረብንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳሩ ግን አምላካችን እግዚአብሔር ወደ ከለከለን ሁሉ፥ ወደ አሞን ልጆች ምድር በያቦቅም ወንዝ አጠገብ ወዳለው ስፍራ ሁሉ በተራራማውም አገር ወዳሉት ከተሞች አልደረስንም። |
በዚያችም ሌሊት ተነሣ፥ ሁለቱን ሚስቶቹንና ሁለቱን ዕቁባቶቹን ዐሥራ አንዱንም ልጆቹን ይዞ የያቦቅን ወንዝ ተሻገረ።
እስራኤልም በሰይፍ መታው፤ ምድሩንም ከአርኖን ጀምሮ እስከ አሞን ልጆች እስከ ያቦቅ ድረስ ወረሰ፤ የአሞንም ልጆች ዳርቻ ኢያዜር ነበረ።
ለሎጥም ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከአሞን ልጆች ምድር ርስት አልሰጥህምና በአሞን ልጆች አቅራቢያ ስትደርስ አትጣላቸው፤ አትውጋቸውም።’
የሴይርን ተራራ ለዔሳው ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታህል እንኳን አልሰጣችሁምና አትጣሉአቸው።
“እግዚአብሔርም አለኝ፦ እኔ አሮኤርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከምድሩ ርስት አልሰጣችሁምና ሞዓባውያንን አትጣላ፤ በሰልፍም አትውጋቸው።
ለሮቤልና ለጋድም ከገለዓድ ምድር ጀምሮ እስከ አርኖን ሸለቆ ድረስ የሸለቆውን እኩሌታ ዳርቻውንም፥ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ እስከ ኢያቦቅ ወንዝ ድረስ፥
በሐሴቦን የተቀመጠው፥ በአርኖንም ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ከሸለቆውም መካከል ጀምሮ የገለዓድን እኩሌታ እስከ ኢያቦቅ ወንዝ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ፤