በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔርና በሸለቆውም ውስጥ ካለችው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ተራራ ድረስ ማንኛዪቱም ከተማ አላመለጠችንም፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉን አሳልፎ በእጃችን ሰጠን።
ዘዳግም 2:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእኛ ከማረክናቸው ከብቶቻቸውና ከከተሞቻቸው ከወሰድነው ምርኮ በቀር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከብቶቻቸውንና ከየከተሞቻቸው ያገኘነውን ምርኮ ግን ለራሳችን አደረግን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከብቶቻቸውንና ከከተሞቻቸው ያገኘነውን ምርኮ ግን ለራሳችን ወሰድን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከብቱን ወሰድን፤ ከተሞችንም በዘበዝን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከብቶቻቸውንና ከከተሞቻቸው ያገኘነውን ብዝበዛ ለራሳችን ወሰድን እንጂ። |
በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔርና በሸለቆውም ውስጥ ካለችው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ተራራ ድረስ ማንኛዪቱም ከተማ አላመለጠችንም፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉን አሳልፎ በእጃችን ሰጠን።
ከሴቶቹና ከጓዙ በቀር እንስሶቹን፥ በከተማዪቱም ያለውን ምርኮ ሁሉ ዘርፈህ ለአንተ ትወስዳለህ፤ አምላክህም እግዚአብሔር የሚሰጥህን የጠላቶችህን ምርኮ ትበላለህ።
በኢያሪኮና በንጉሥዋም እንዳደረግህ እንዲሁ በጋይና በንጉሥዋ ታደርጋለህ፤ የከብቱን ምርኮ ግን ለራሳችሁ ትዘርፋላችሁ፤ ከከተማዪቱም በስተኋላ ይከብቧት ዘንድ ጦር ላክ” አለው።