ዘዳግም 2:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ‘አንተ ዛሬ የሞዓብን ዳርቻ አሮኤርን ታልፋለህ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሞዓብ ዳርቻ ዔርን ዛሬውኑ ታልፋላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘አንተ ዛሬ የሞዓብን ዳርቻ ዔርን ታልፋለህ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘የሞአብ ክልል በሆነው በዔር በኩል ዛሬውኑ ማለፍ አለባችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ ዛሬ የሞዓብን ዳርቻ ዔርን ታልፋለህ፤ |
ከዚያም ተጕዘው ከአሞራውያን ዳርቻ በሚወጣው ምድረ በዳ ውስጥ በአርኖን ማዶ ሰፈሩ፤ አርኖን በሞዓብና በአሞራውያን መካከል ያለ የሞዓብ ዳርቻ ነውና።
ሴዎንም እስራኤል በወሰኑ ላይ ያልፉ ዘንድ አልፈቀደም፤ ሴዎንም ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፤ እስራኤልንም ለመውጋት ወደ ምድረ በዳ ወጣ፤ ወደ ኢያሶንም መጣ፤ እስራኤልንም ተዋጋቸው።
“እግዚአብሔርም አለኝ፦ እኔ አሮኤርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከምድሩ ርስት አልሰጣችሁምና ሞዓባውያንን አትጣላ፤ በሰልፍም አትውጋቸው።
እስራኤልም በቃዴስ ተቀመጠ። በምድረ በዳም በኩል አለፈ፤ የኤዶምያስንና የሞዓብንም ምድር ዞሩ፤ ከሞዓብ ምድርም በምሥራቅ በኩል መጡ፤ በአርኖንም ማዶ ሰፈሩ፤ አርኖንም የሞዓብ ድንበር ነበረና ወደ ሞዓብ ድንበር አልገቡም።