ዘዳግም 19:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የነፍሰ ገዳይ ሕግ ይህ ነው፤ ቀድሞ ጠላቱ ሳይሆን ባልንጀራውን ሳያውቅ የገደለ ወደዚያ ሸሽቶ በሕይወት ይኑር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተንኰል ሳይሆን ድንገት ሳያስበው ባልንጀራውን ገድሎ ሕይወቱን ለማትረፍ ለሚሸሽ ሰው መመሪያው የሚከተለው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተንኰል ሳይሆን ድንገት ሳያስበው ባልንጀራውን ገድሎ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ በመግባት ሕይወቱን ለማትረፍ ለሚሸሽ ሰው መመሪያው የሚከተለው ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው ቀድሞ ጠላት ያልነበረውን አንድ ሰው የገደለው ሆን ብሎ በማሰብ ሳይሆን በአጋጣሚ አደጋ ምክንያት ሆኖ ከተገኘ አምልጦ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ በመግባት ሕይወቱን ያትርፍ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የነፍሰ ገዳይ ወግ ይህ ነው፤ አስቀድሞ ጠላቱ ሳይሆን ባልንጀራውን ሳያስብ የገደለ ወደዚያ ሸሽቶ በሕይወት ይኑር። |
ያችም ሴት፥ “ለመግደል ባለ ደሞች እንዳይበዙ፤ ልጄንም እንዳይገድሉብኝ ንጉሥ ፈጣሪው እግዚአብሔርን ያስብ” አለች። እርሱም፥ “የልጅሽስ አንዲት የራሱ ጠጕር በምድር ላይ እንዳትወድቅ ሕያው እግዚአብሔርን” አላት።
አስቀድሞ ሳኦል ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስራኤልን የምታወጣና የምታገባ አንተ ነበርህ፤ አምላክህ እግዚአብሔርም፦ ሕዝቤን እስራኤልን አንተ ትጠብቃለህ፤ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ አለቃ ትሆናለህ” አለህ።
ከቀድሞም ጀምሮ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅታለች፤ ለንጉሥም ተበጅታለች፤ ጥልቅና ሰፊም አድርጎአታል፤ እሳትና ብዙ ማገዶ ተከምሮአል፤ የእግዚአብሔርም ቍጣ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃጥለዋል።
ነፍሰ ገዳዩ በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስከሚቆም ድረስ እንዳይሞት፥ ከተሞቹ ከደም ተበቃይ የመማፀኛ ከተሞች ይሁኑላችሁ።
ለአንተም መንገድህን ታዘጋጃለህ፤ አምላክህም እግዚአብሔር የሚያወርስህን ምድር ከሦስት አድርገህ ትከፍላለህ፤ ለነፍሰ ገዳይም ሁሉ መማጸኛ ይሁን።
ሰው ከባልንጀራው ጋር እንጨት ሊለቅም ወደ ዱር ቢሄድ፥ ዛፉንም ሲቈርጥ ምሳሩ ከእጁ ቢወድቅ፥ ብረቱም ከእጄታው ቢወልቅ፥ በባልንጀራውም ላይ ቢወድቅና ቢገድለው፥ ከእነዚህ ከተሞች በአንዲቱ ተማጥኖ በሕይወት ይኖራል፤
ባለ ደሙ ነፍሰ ገዳዩን በልቡ ተናድዶ እንዳያሳድደው መንገዱም ሩቅ ስለሆነ አግኝቶ እንዳይገድለው፥ አስቀድሞ ጠላቱ አልነበረምና ሞት አይገባውም።
ትናንት፥ ከትናት በስቲያም ጠላቱ ያልሆነውን ባልንጀራውን ሳያውቅ የገደለ ገዳዩ ይማፀንባቸው ዘንድ፥ ከእነዚህም ከተሞች በአንዲቱ ተማፅኖ በሕይወት ይኖር ዘንድ፤
በእናንተና በታቦቱ መካከል ያለው ርቀት በስፍር ሁለት ሺህ ክንድ ያህል ይሁን፤ በዚህ መንገድ በፊት አልሄዳችሁበትምና የምትሄዱበትን መንገድ እንድታውቁ ወደ ታቦቱ አትቅረቡ።”