La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 19:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ሰ​ጥህ በም​ድ​ርህ መካ​ከል ሦስት ከተ​ሞ​ችን ለራ​ስህ ትለ​ያ​ለህ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር አማካይ ስፍራ፣ ሦስት ከተሞችን ለራስህ ለይ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አምላክህ ጌታ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር አማካይ ስፍራ፥ ሦስት ከተሞችን ለራስህ ትለያለህ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አምላክህ እግዚአብሔር እንድትኖርባት የሚሰጥህን ምድር ለሦስት ትከፍልና በያንዳንዱ ክፍል አንዳንድ ከተማ የተለየ ታደርጋለህ፤ ነፍሰ ገዳይም ይሸሽባቸው ዘንድ ወደ እነዚያ የሚወስዱትን መንገዶች ታዘጋጃለህ፤ ከዚያ በኋላ አንድ ነፍሰ ገዳይ ሕይወቱን ለማትረፍ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ ሸሽቶ ይሂድ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ በምድርህ መካከል ሦስት ከተሞችን ለራስህ ትለያለህ።

Ver Capítulo



ዘዳግም 19:2
7 Referencias Cruzadas  

ሳይ​ፈ​ቅድ ቢመ​ታው፥ ባይ​ሸ​ም​ቅ​በ​ትም፥ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድን​ገት በእጁ ቢጥ​ለው፥ ገዳዩ የሚ​ሸ​ሽ​በ​ትን ስፍራ እኔ አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ።


ለአ​ን​ተም መን​ገ​ድ​ህን ታዘ​ጋ​ጃ​ለህ፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ወ​ር​ስ​ህን ምድር ከሦ​ስት አድ​ር​ገህ ትከ​ፍ​ላ​ለህ፤ ለነ​ፍሰ ገዳ​ይም ሁሉ መማ​ጸኛ ይሁን።


“በዚ​ያም ዘመን እን​ዲህ ብዬ አዘ​ዝ​ኋ​ችሁ፦ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ችን ምድር ርስት አድ​ርጎ ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋል፤ መሣ​ሪ​ያ​ች​ሁን ይዛ​ችሁ እና​ንተ አር​በ​ኞች ሁሉ በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ትሻ​ገ​ራ​ላ​ችሁ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይ​ቻ​ልም፤ በእ​ርሱ ለተ​ማ​ፀን ተጠ​ብ​ቆ​ልን ባለ ተስ​ፋ​ች​ንም ማመ​ንን ላጸ​ናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን።