ዘዳግም 15:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከባዕድ ግን በእርሱ ዘንድ ያለህን ሁሉ መቀበል ትችላለህ፤ በወንድምህ ላይ ያለውን ሁሉ ግን ተውለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለባዕድ ያበደርኸውን መጠየቅ ትችላለህ፤ ወንድምህ ከአንተ የተበደረውን ማንኛውንም ዕዳ ግን ተወው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለባዕድ ያበደርከውን መጠየቅ ትችላለህ፤ ወንድምህ ከአንተ የተበደረውን ማናቸውንም ዕዳ ግን ተወው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለውጪ አገር ሰው ያበደርከው ብድር እንዲመለስልህ መጠየቅ ትችላለህ፤ ለማንኛውም እስራኤላዊ ወገንህ ያበደርከው ገንዘብ ግን እንዲመለስልህ መጠየቅ የለብህም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእንግዳ ላይ ያበደርኸውን መፈለግ ትችላለህ፤ በወንድምህ ላይ ያለውን ሁሉ ግን እጅህ ይተወዋል። |
ለምሕረቱም የሚገባ ትእዛዝ ይህ ነው፤ ባልንጀራህ ወይም ወንድምህ የሚከፍልህን ገንዘብ ሁሉ አትከፈል፤ የአምላክህ የእግዚአብሔር ምሕረት ተብላለችና።
ለእንግዳው በወለድ አበድር፤ ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ልትወርሳት በምትገባባት ምድር በሥራህ ሁሉ ይባርክህ ዘንድ ለወንድምህ በወለድ አታበድር።
“ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልህ ጊዜ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ፈጽሞ ይሻዋልና፥ ኀጢአትም ይሆንብሃልና መክፈሉን አታዘግይ።