La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 15:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ሱ​ንም አር​ነት ባወ​ጣ​ኸው ጊዜ የም​ን​ደ​ኝ​ነ​ቱን ሥራ ሁለት ዕጥፍ አድ​ርጎ ስድ​ስት ዓመት አገ​ል​ግ​ሎ​ሃ​ልና አያ​ስ​ጨ​ን​ቅህ፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ት​ሠ​ራው ሁሉ ይባ​ር​ክ​ሃል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አገልጋይህን ዐርነት ማውጣቱ ከባድ መስሎ አይታይህ፤ የስድስት ዓመት አገልግሎቱ፣ አንድ የቅጥር ሠራተኛ የሚሰጠው አገልግሎት ዕጥፍ ነውና። አምላክህ እግዚአብሔር በምታደርገው ነገር ሁሉ ይባርክሃል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የአገልጋይህን የስድስት ዓመት አገልግሎቱ፥ አንድ የቅጥር ሠራተኛ ከሚሰጠው አገልግሎት ዕጥፍ ነውና፤ እርሱን ነጻ ማውጣቱ ከባድ መስሎ አይታይህ። ጌታ እግዚአብሔር በምታደርገው ነገር ሁሉ ይባርክሃል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እርሱንም ነጻ ባወጣኸው ጊዜ አንድ ተቀጣሪ ለስድስት ዓመት ከሚሰጥህ እጥፍ አገልግሎት ስለ ሰጠህ ቅር አይበልህ። እንግዲህ ይህን አድርግ፤ እግዚአብሔርም በምትሠራው ሁሉ ይባርክሃል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱንም አርነት ባወጣኸው ጊዜ የምንደኝነቱን ሥራ ሁለት እጥፍ አድርጎ ስድስት ዓመት አገልግሎሃልና አይክበድህ፤ አምልካህም እግዚአብሔር በምትሠራው ሁሉ ይባርክሃል።

Ver Capítulo



ዘዳግም 15:18
6 Referencias Cruzadas  

አሁ​ንም እን​ዲህ እላ​ለሁ፤ በሦ​ስት ዓመት ውስጥ እንደ ምን​ደኛ ዓመት የሞ​ዓብ ክብር ከብዙ ሀብ​ትዋ ጋር ይዋ​ረ​ዳል፤ በቍ​ጥ​ርም ጥቂት ይቀ​ራል፤ ክብ​ር​ዋም አይ​ገ​ኝም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገና እን​ዲህ ብሎ​ኛ​ልና፥ “እንደ ምን​ደኛ ዓመት በአ​ንድ ዓመት ውስጥ የቄ​ዳር ልጆች ክብር ሁሉ ይጠ​ፋል፤


እጅ​ህን በም​ት​ጥ​ል​በት ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ​ዚህ በሥ​ራህ ሁሉ ይባ​ር​ክ​ሃ​ልና ፈጽ​መህ ስጠው፤ የለ​መ​ነ​ህ​ንም ያህል አበ​ድ​ረው፤ በሰ​ጠ​ኸ​ውም ጊዜ በል​ብህ አት​ጸ​ጸት።


አንተ ወስፌ ወስ​ደህ በቤ​ትህ በር ላይ ጆሮ​ውን ትበ​ሳ​ዋ​ለህ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ባሪያ ይሆ​ን​ል​ሃል። በሴት ባሪ​ያ​ህም ደግሞ እን​ዲሁ ታደ​ር​ጋ​ለህ።


“ላም​ህና በግህ የወ​ለ​ዱ​ትን ተባት የሆ​ነ​ውን በኵ​ራት ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትቀ​ድ​ሳ​ለህ፤ በበ​ሬህ በኵ​ራት አት​ሥ​ራ​በት፤ የበ​ግ​ህ​ንም በኵ​ራት አት​ሸ​ልት።