ዘዳግም 15:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ወስፌ ወስደህ በቤትህ በር ላይ ጆሮውን ትበሳዋለህ፤ ለዘለዓለምም ባሪያ ይሆንልሃል። በሴት ባሪያህም ደግሞ እንዲሁ ታደርጋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጆሮውን ከቤትህ መዝጊያ ላይ በማስደገፍ በወስፌ ትበሳዋለህ፤ ከዚያም ዕድሜ ዘመኑን አገልጋይህ ይሆናል። በሴት አገልጋይህም ላይ እንደዚሁ አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጆሮውን ከቤትህ መዝጊያ ላይ በማስደገፍ በወስፌ ትበሳዋለህ፤ ከዚያም ዕድሜ ልኩን አገልጋይህ ይሆናል። በሴት አገልጋይህም ላይ እንደዚሁ አድርግ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ከሆነ ወደ ቤትህ ደጃፍ ወስደህ ጆሮውን በወስፌ ብሳው፤ ከዚያም በኋላ እስከ ዕድሜው ፍጻሜ ድረስ የአንተ ባሪያ ይሆናል፤ ለሴት ባሪያህም ቢሆን ይህንኑ አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ ወስፌ ወስደህ በቤትህ በር ላይ ጆሮውን ትበሳዋለህ፥ ለዘላለምም ባሪያ ይሆንሃል። በሴት ባሪያህ ደግሞ እንዲሁ ታደርጋለህ። |
ጌታው ወደ ቤተ እግዚአብሔር ፈራጆች ይውሰደው፤ ወደ ደጁም፥ ወደ መቃኑም አቅርቦ አፍንጫውን በወስፌ ይብሳው፤ ለዘለዓለምም ባሪያው ይሁነው።
እርሱንም አርነት ባወጣኸው ጊዜ የምንደኝነቱን ሥራ ሁለት ዕጥፍ አድርጎ ስድስት ዓመት አገልግሎሃልና አያስጨንቅህ፤ አምላክህም እግዚአብሔር በምትሠራው ሁሉ ይባርክሃል።
ሐና ግን ከእርሱ ጋር አልወጣችም። ለባልዋም፥ “ሕፃኑን ጡት እስከ አስጥለው፥ ከእኔም ጋር እስኪወጣና በእግዚአብሔር ፊት እስኪታይ ድረስ አልወጣም፤ በዚያም ለዘለዓለም ይኖራል” ብላዋለችና።