ዘዳግም 13:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትፈልጋለህ ትመረምራለህም፤ ትጠይቃለህም፤ እነሆም፥ እውነት ቢሆን፥ ይህም ክፉ ነገር በመካከልህ እንደ ተደረገ ርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጕዳዩን አጣራ፤ መርምር፤ በሚገባም ተከታተል፤ ነገሩ እውነት ሆኖ ከተገኘና ይህ አስጸያፊ ነገር በመካከልህ መፈጸሙ ከተረጋገጠ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጉዳዩን አጣራ፤ መርምር፤ በሚገባም ተከታተል፤ ነገሩ እውነት ሆኖ ከተገኘና ይህ አስጸያፊ ነገር በመካከልህ መፈጸሙ ከተረጋገጠ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን በምትሰማበት ጊዜ ስለ ጉዳዩ ጠይቀህ ጠለቅ አድርገህ መርምር፤ ይህ አስከፊ የሆነው ጉዳይ በመካከላችሁ መደረጉ በእውነት ከተረጋገጠ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትፈልጋለህ፥ ትመረምራለህም፥ ትጠይቃለህም፤ እነሆም፥ እውነት ቢሆን፥ ይህም ክፉ ነገር በመካከልህ እንደ ተደረገ እርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥ |
ክፋተኞች ሰዎች ከእናንተ ዘንድ ወጥተው፦ ሄደን የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብለው የከተማቸውን ሰዎች አሳቱ ሲሉ ወሬ ብትሰማ፥
ቢያወሩልህም ብትሰማም፥ ያን ፈጽመህ መርምር፤ እነሆም፥ እውነት ቢሆን፥ በእስራኤልም መካከል እንዲህ ያለ ርኵሰት እንደ ተሠራ ርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥