“እንደ ተናገረው ተስፋ ሁሉ ለሕዝቡ ለእስራኤል ዕረፍትን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን፥ በባሪያው በሙሴ ቃል ከተናገረው ከመልካም ቃል ሁሉ ያጐደለው አንድም ቃል የለም።
ዘዳግም 12:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ማረፊያና ርስት እስከ ዛሬ ድረስ አልደረሳችሁምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም ማረፊያ ወደ ሆነውና አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ርስት ገና አልደረሳችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክንያቱም ማረፊያ ወደ ሆነውና ጌታ አምላካችሁ ወደ የሚሰጣችሁ ርስት ገና አልደረሳችሁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደሚሰጣችሁና በሰላም ዕረፍት አድርጋችሁ ወደምትኖሩባት ርስት ገና አልገባችሁም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ዕረፍትና ርስት እስከ ዛሬ ድረስ አልገባችሁምና። |
“እንደ ተናገረው ተስፋ ሁሉ ለሕዝቡ ለእስራኤል ዕረፍትን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን፥ በባሪያው በሙሴ ቃል ከተናገረው ከመልካም ቃል ሁሉ ያጐደለው አንድም ቃል የለም።
ዳዊትም እንዲህ አለ፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ዕረፍት ሰጥቶአል፤ በኢየሩሳሌምም ለዘለዓለም ይቀመጣል።
ስለዚህ አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር ከሚከብቡህ ጠላቶችህ ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ባሳረፈህ ጊዜ፥ የዐማሌቅን ዝክረ ስሙን ከሰማይ በታች አጥፋው፤ ይህንም አትርሳ።
ይኸውም እግዚአብሔር እንደ እናንተ፥ ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፍ ድረስ፥ እነርሱም ደግሞ በዮርዳኖስ ማዶ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ ነው። ከዚያም በኋላ ሁላችሁ ወደ ሰጠኋችሁ ርስት ትመለሳላችሁ።
እግዚአብሔርም እናንተ በተናገራችሁት ምክንያት ተቈጣኝ፤ ዮርዳኖስንም እንዳልሻገር፥ አምላክህም እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ወደሚሰጥህ ወደ መልካሚቱ ምድር እንዳልገባ ማለ።
እግዚአብሔርም ለሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያሱም ለእስራኤል እንደ ክፍላቸው በየነገዳቸው ርስት አድርጎ ምድሪቱን ሰጣቸው፤ ምድሪቱም ከጦርነት ዐረፈች።