La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 11:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ መካ​ከል ምድር አፍ​ዋን ከፍታ እነ​ር​ሱ​ንና ቤተ ሰቦ​ቻ​ቸ​ውን፥ ድን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ለእ​ነ​ር​ሱም የነ​በ​ራ​ቸ​ውን ሁሉ በዋ​ጠ​ቻ​ቸው በሮ​ቤል ልጅ በኤ​ል​ያብ ልጆች በዳ​ታ​ንና በአ​ቤ​ሮን ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የሮቤል ልጅ የኤልያብ ልጆች የሆኑትን ዳታንና አቤሮንን ከነቤተ ሰቦቻቸው፣ ከነድንኳናቸውና ከነእንስሳታቸው በመላው እስራኤል መካከል ምድር እንዴት አፏን ከፍታ እንደ ዋጠቻቸው እነርሱ አላዩም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የሮቤል ልጅ የኤልያብ ልጆች የሆኑትን ዳታንና አቤሮንን ከነቤተሰቦቻቸው፥ ከነድንኳናቸውና ከነእንስሳታቸው በመላው እስራኤል መካከል ምድር እንዴት አፏን ከፍታ እንደዋጠቻቸው እነርሱ አላዩም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከሮቤል ነገድ ወገን የኤልያብ ልጆች በሆኑት በዳታንና በአቤሮን ላይ ያደረገውን አስታውሱ፤ እስራኤላውያን ሁሉ በዐይናቸው እያዩ መሬት ተከፍታ እነርሱንና ቤተሰቦቻቸውን፥ ድንኳኖቻቸውንና ሕይወት ያለውና የእነርሱ የነበረውን ሁሉ ዋጠቻቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በእስራኤልም ሁሉ መካከል ምድር አፍዋን ከፍታ እነርሱንና ቤተሰቦቻቸውን ድንኳኖቻቸውንም ለእነርሱም የነበራቸውን ሁሉ በዋጠቻቸው በሮቤል ልጅ በኤልያብ ልጆች በዳታንና በአቤሮን ያደረገውን ላላወቁትና ላላዩት ልጆቻችሁ አልነግራቸውምና እናንተ ዛሬ እወቁ።

Ver Capítulo



ዘዳግም 11:6
9 Referencias Cruzadas  

የና​ሱን ደጆች ሰብ​ሮ​አ​ልና፥ የብ​ረ​ቱ​ንም መወ​ር​ወ​ሪያ ቀጥ​ቅ​ጦ​አ​ልና።


ከበ​ደ​ላ​ቸው ጎዳና ተቀ​በ​ላ​ቸው፥ በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ተሠ​ቃ​ይ​ተ​ዋ​ልና።


ምድር ደነ​ገ​ጠች፤ ታወ​ከ​ችም፤ ምድር ጐሰ​ቈ​ለች፤ ተነ​ዋ​ወ​ጠ​ችም።


የቆሬ ልጆች ግን አል​ሞ​ቱም።


“አባ​ታ​ችን በም​ድረ በዳ ሞተ፤ በራሱ ኀጢ​አት ሞተ እንጂ ከቆሬ ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ በተ​ሰ​በ​ሰቡ ወገን መካ​ከል አል​ነ​በ​ረም፤ ወን​ዶ​ችም ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​ትም።


ወደ​ዚህ ስፍራ እስ​ክ​ት​መጡ ድረስ በም​ድረ በዳ ያደ​ረ​ገ​ላ​ች​ሁን ሁሉ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ረ​ጋ​ቸ​ውን ታላ​ላቅ ሥራ​ዎች ሁሉ ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ አይ​ተ​ዋ​ልና።