La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 11:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነ​ር​ሱም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ፥ ከፀ​ሐይ መግ​ቢያ ካለ​ችው መን​ገድ በኋላ በዓ​ረባ በተ​ቀ​መ​ጡት በከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን ምድር፥ በጌ​ል​ጌላ ፊት ለፊት በረ​ዥሙ ዛፍ አጠ​ገብ ናቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነዚህ ተራሮች የሚገኙት ከዮርዳኖስ ማዶ ፀሓይ በምትጠልቅበት አቅጣጫ ካለው መንገድ በስተምዕራብ በዓረባ በሚኖሩ የከነዓናውያን ምድር ውስጥ ከጌልገላ ፊት ለፊት፣ በሞሬ ታላላቅ ዛፎች አጠገብ አይደለምን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነዚህ ተራሮች የሚገኙት ከዮርዳኖስ ማዶ ፀሓይ በምትጠልቅበት አቅጣጫ ካለው መንገድ በስተ ምዕራብ በዓረባ በሚኖሩ የከነዓናውያን ምድር ውስጥ ከጌልገላ ፊትለፊት፥ በሞሬ ታላላቅ ዛፎች አጠገብ አይደለምን?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነዚህም ተራራዎች ከዮርዳኖስ ማዶ በስተምዕራብ በኩል፥ በአራባ በሚኖሩት በከነዓናውያንም ምድር በጌልገላ ፊት ለፊት ከሞሬ ዛፍ አጠገብ የሚገኙ ናቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ፥ ከፀሐይ መግቢያ ካለችው መንገድ በኋላ፥ በዓረባ በተቀመጡት በከነዓናውያን ምድር፥ በጌልገላ ፊት ለፊት በሞሬ የአድባር ዛፍ አጠገብ ናቸው።

Ver Capítulo



ዘዳግም 11:30
6 Referencias Cruzadas  

አብ​ራ​ምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ታላቁ ዛፍ ድረስ በዚ​ያች ምድር አለፈ፤ የከ​ነ​ዓን ሰዎ​ችም በዚ​ያን ጊዜ በዚ​ያች ምድር ነበሩ።


ከቤት ጌል​ጋ​ልና ከጌባ፥ ከአ​ዝ​ማ​ዊ​ትም እርሻ መዘ​ም​ራኑ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዙርያ ለራ​ሳ​ቸው መን​ደ​ሮች ሠር​ተ​ዋ​ልና።


ሕዝ​ቡም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ወጡ፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም በም​ሥ​ራቅ በኩል በጌ​ል​ገላ ሰፈሩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “ዛሬ የግ​ብ​ፅን ተግ​ዳ​ሮት ከእ​ና​ንተ ላይ አስ​ወ​ግ​ጃ​ለሁ” አለው፤ ስለ​ዚህ የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌል​ገላ ተብሎ ተጠራ።


ጌዴ​ዎን የተ​ባ​ለ​ውም ይሩ​በ​ኣል ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሕዝብ ሁሉ ማል​ደው ተነሡ፤ በአ​ሮ​ኤድ ምንጭ አጠ​ገብ ሰፈሩ፤ የም​ድ​ያ​ምም ሰፈር ከእ​ነ​ርሱ ወደ ሰሜን በኩል በሞሬ ኮረ​ብታ አጠ​ገብ በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ነበረ።


ይህ​ንም ነገር ለኢ​ዮ​አ​ታም በነ​ገ​ሩት ጊዜ፥ ሄዶ በገ​ሪ​ዛን ተራራ ራስ ላይ ቆመ፤ ድም​ፁ​ንም አን​ሥቶ አለ​ቀሰ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “የሰ​ቂማ ሰዎች ሆይ! ስሙኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይስ​ማ​ችሁ።