“ከማይነቅዝ ዕንጨትም የምስክሩን ታቦት ሥራ፤ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን።
ዘዳግም 10:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከማይነቅዝ እንጨትም ታቦቱን ሠራሁ፤ እንደ ፊተኞችም ሁለት የድንጋይ ጽላት ቀረፅሁ፤ ወደ ተራራውም ወጣሁ፤ ሁለቱም ጽላት በእጄ ነበሩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ከግራር ዕንጨት ታቦት ሠራሁ፤ እንደ ፊተኞቹ ያሉ ሁለት የድንጋይ ጽላት ቀረጽሁ፤ ሁለቱንም ጽላት በእጆቼ ይዤ ወደ ተራራው ወጣሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እኔም ከግራር እንጨት ታቦትን ሠራሁ፥ እንደ ቀድሞዎቹም ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠረብሁ፥ ሁለቱንም ጽላቶች በእጄ ይዤ ወደ ተራራው ወጣሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለዚህም እኔ ከግራር እንጨት ታቦትን ሠራሁ፤ እንደ ፊተኞቹ ያሉትንም የድንጋይ ጽላቶች በመቅረጽ አዘጋጀሁ፤ እነርሱንም በእጄ ይዤ ወደ ተራራው ወጣሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከግራርም እንጨት ታቦትን ሠራሁ፥ እንደ ፊተኞችም ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠረብሁ፤ ሁለቱንም ጽላቶች በእጄ ይዤ ወደ ተራራው ወጣሁ። |
“ከማይነቅዝ ዕንጨትም የምስክሩን ታቦት ሥራ፤ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን።
ሙሴም እንደ ፊተኞቹ አድርጎ ሁለት የድንጋይ ጽላት ቀረጸ፤ ሁለቱንም የድንጋይ ጽላት በእጁ ወሰደ፤ በነጋውም ማልዶ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ወደ ሲና ተራራ ወጣ፤
“በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር እንደ ፊተኞች ያሉትን ሁለት የድንጋይ ጽላት ለአንተ ቀርፀህ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፤ ለአንተም የእንጨት ታቦት ሥራ፤
በውስጥዋም የወርቅ ማዕጠንትና ሁለንተናዋን በወርቅ የለበጡአት፥ የኪዳን ታቦት፥ መና ያለባት የወርቅ መሶብና የለመለመችው የአሮን በትር፥ የኪዳኑም ጽላት ነበሩባት።