ከአንድ ሰው ዛቻ የተነሣ ሺህ ሰዎች ይሸሻሉ፤ እናንተም በተራራ ራስ ላይ እንዳለ ምሰሶ፥ በኮረብታም ላይ እንዳለ ምልክት ሆናችሁ እስክትቀሩ ድረስ፥ ከአምስት ሰዎች ዛቻ የተነሣ ብዙዎች ይሸሻሉ።”
ዘዳግም 1:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም፦ እኔ ከእናንተ ጋር አይደለሁምና በጠላቶቻችሁ ፊት እንዳትወድቁ አትውጡ፤ አትዋጉም በላቸው አለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ግን፣ “ ‘እኔ ከእናንተ ጋራ አልሆንምና ወጥታችሁ እንዳትዋጉ፤ በጠላቶቻችሁ ድል ትነሣላችሁ’ ብለህ ንገራቸው” አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታም፦ ‘እኔ በእናንተ መካከል አይደለሁምና በጠላቶቻችሁ ፊት እንዳትወድቁ አትውጡ፥ አትዋጉም በላቸው’ አለኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር ግን ‘እኔ ከእናንተ ጋር ስለማልሆን ለመዋጋት አትውጡ፤ ይህ ካልሆነ ጠላቶቻችሁ ድል ይመቱአችኋል’ በላቸው አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም፦ እኔ በእናንተ መካከል አይደለሁምና በጠላቶቻችሁ ፊት እንዳትወድቁ አትውጡ፥ አትዋጉም በላቸው አለኝ። |
ከአንድ ሰው ዛቻ የተነሣ ሺህ ሰዎች ይሸሻሉ፤ እናንተም በተራራ ራስ ላይ እንዳለ ምሰሶ፥ በኮረብታም ላይ እንዳለ ምልክት ሆናችሁ እስክትቀሩ ድረስ፥ ከአምስት ሰዎች ዛቻ የተነሣ ብዙዎች ይሸሻሉ።”
ፊቴንም አከብድባችኋለሁ፤ በጠላቶቻችሁም ፊት ትወድቃላችሁ፤ የሚጠሏችሁም ያሸንፉአችኋል። ማንም ሳያሳድዳችሁ ትሸሻላችሁ።
ከዚህም በኋላ ተዋጉአቸው፤ እስራኤልም በፍልስጥኤማውያን ፊት ወደቁ፤ ሁሉም እያንዳንዳቸው ወደ ድንኳናቸው ሸሹ፤ እጅግም ታላቅ ግድያ ሆነ፤ ከእስራኤልም ሠላሳ ሺህ እግረኞች ወደቁ።
ፍልስጥኤማውያንም እስራኤልን ለመውጋት ተሰለፉ፤ እስራኤልም ሸሹ፤ በፍልስጥኤማውያንም ፊት ድል ሆኑ፤ ጦርነት በተደረገበትም ስፍራ ከእስራኤል አራት ሺህ ሰዎች ተገደሉ።