ዘዳግም 1:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ብቻዬን ድካማችሁን፥ ሸክማችሁንም፥ ክርክራችሁንም እሸከም ዘንድ እንዴት እችላለሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ ችግራችሁን፣ ሸክማችሁንና ክርክራችሁን ሁሉ ብቻዬን እንዴት አድርጌ መሸከም እችላለሁ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ብቻዬን ድካምችሁን፥ ሸክማችሁንም፥ ክርክራችሁንም እሸከም ዘንድ እንዴት እችላለሁ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በመካከላችሁ የሚነሣውን ጠብና ክርክር ለማስወገድ ይህን ከባድ ኀላፊነት ብቻዬን እንዴት ልሸከም እችላለሁ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ብቻዬን ድካምችሁን ሸክማችሁንም ክርክራችሁንም እሸከም ዘንድ እንዴት እችላለሁ? |
ከእናንተ ከየነገዳችሁ ጥበበኞች፥ አስተዋዮችም፥ ዐዋቂዎችም የሆኑትን ሰዎች አምጡ፤ እኔም በላያችሁ አለቆች አደርጋቸዋለሁ።