አሞጽ 8:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከባሕርም እስከ ባሕር ድረስ፥ ከሰሜንም እስከ ምሥራቅ ድረስ ይቅበዘበዛሉ፤ የእግዚአብሔርንም ቃል ለመሻት ይርዋርዋጣሉ፤ አያገኙትምም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል በመሻት፣ ከባሕር ወደ ባሕር፣ ከሰሜን ወደ ምሥራቅ ይንከራተታሉ፤ ነገር ግን አያገኙትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከባሕርም እስከ ባሕር ድረስ፥ ከሰሜንም እስከ ምሥራቅ ድረስ ይቅበዘበዛሉ፤ የጌታን ቃል ለመሻት ይሯሯጣሉ፥ ነገር ግን አያገኙትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡ ሁሉ ከሰሜን እስከ ደቡብ፥ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ የእግዚአብሔርንም ቃል ለማግኘት በሁሉ ቦታ ይንከራተታሉ፤ ነገር ግን አያገኙም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከባሕርም እስከ ባሕር ድረስ፥ ከሰሜንም እስከ ምሥራቅ ድረስ ይቅበዘበዛሉ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ለመሻት ይርዋርዋጣሉ፥ አያገኙትምም። |
“የሰው ልጅ ሆይ! ለእስራኤል ሽማግሌዎች ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔን ትጠይቁ ዘንድ መጥታችኋልን? እኔ ሕያው ነኝ! አልመልስላችሁም፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ቍርባናችሁን በአቀረባችሁ ጊዜ፥ ልጆቻችሁንም በእሳት ባሳለፋችሁ ጊዜ፥ እስከ ዛሬ ድረስ በዐሳባችሁ ሁሉ ረከሳችሁ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! እኔስ እመልስላችኋለሁን? እኔ ሕያው ነኝ! አልመልስላችሁም፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
እግዚአብሔርንም ለመሻት ከበጎቻቸውና ከላሞቻቸው ጋር ይሄዳሉ፤ ነገር ግን እርሱ ከእነርሱ ተለይቶአልና አያገኙትም።
ብላቴናው ሳሙኤልም በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር፤ በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ክቡር ነበረ፤ ራእይም አይገለጥም ነበር።