ሐዋርያት ሥራ 9:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳውልም በራእይ ሐናንያ የሚባል ሰው ወደ እርሱ ገብቶ ያይ ዘንድ እጁን ሲጭንበት አየ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ሐናንያ የሚባል ሰው እርሱ ወዳለበት መጥቶ እጁን እንደሚጭንበትና ዐይኑ እንደሚበራለት በራእይ አይቷል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ እርሱ ይጸልያልና፤ ሐናንያ የሚሉትም ሰው ገብቶ ደግሞ እንዲያይ እጁን ሲጭንበት አይቶአል፤” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳውልም ዐይኖቹ እንደገና ማየት እንዲችሉ ሐናንያ የተባለ ሰው ወደ እርሱ ገብቶ እጁን ሲጭንበት በራእይ አየ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ እርሱ ይጸልያልና፤ ሐናንያ የሚሉትም ሰው ገብቶ ደግሞ እንዲያይ እጁን ሲጭንበት አይቶአል” አለው። |
በደማስቆም ስሙን ሐናንያ የሚሉት አንድ ደቀ መዝሙር ነበር፤ ጌታም በራእይ ተገልጦ፥ “ሐናንያ” ብሎ ጠራው፤ እርሱም፥ “አቤቱ፥ እነሆኝ” አለ።