ከከተማም ወደ ውጭ ጐትተው አውጥተው ወገሩት፤ የሚወግሩት ሰዎችም ልብሳቸውን ሳውል በሚባል ጐልማሳ እግር አጠገብ አስቀመጡ።
ሐዋርያት ሥራ 9:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳውል ግን የጌታን ደቀ መዛሙርት ለመግደል ገና እየዛተ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳውል ግን የጌታን ደቀ መዛሙርት ለመግደል አሁንም እየዛተ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሄደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳውል ግን የጌታን ደቀ መዛሙርት እንዲገድላቸው ገና እየዛተ ወደ ሊቀ ካህናት ሄደ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ሳውል የጌታን ደቀ መዛሙርት ለመግደል ገና እየዛተ ወደ ካህናት አለቃው ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳውል ግን የጌታን ደቀ መዛሙርት እንዲገድላቸው ገና እየዛተ ወደ ሊቀ ካህናት ሄደ፥ |
ከከተማም ወደ ውጭ ጐትተው አውጥተው ወገሩት፤ የሚወግሩት ሰዎችም ልብሳቸውን ሳውል በሚባል ጐልማሳ እግር አጠገብ አስቀመጡ።
ሳውል ግን ገና አብያተ ክርስቲያናትን ይቃወም ነበር፤ የሰውንም ቤት ሁሉ ይበረብር ነበር፤ ወንዶችንም ሴቶችንም እየጐተተ ወደ ወኅኒ ቤት ያስገባቸው ነበር።
ከሐዋርያት ሁሉ እኔ አንሣለሁና፤ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ስለ አሳደድሁ ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ፥
በአይሁድ ሥርዐት ውስጥ በነበርሁ ጊዜ፥ የነበረውን የቀድሞ ሥራዬን ሰምታችኋል፤ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እጅግ አሳድድና መከራ አጸናባቸው ነበር።