ሐዋርያት ሥራ 8:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያችም ከተማ ታላቅ ደስታ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ የተነሣም በከተማዪቱ ታላቅ ደስታ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያችም ከተማ ታላቅ ደስታ ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በዚያች ከተማ ታላቅ ደስታ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያችም ከተማ ታላቅ ደስታ ሆነ። |
አሕዛብም ይህን ሰምተው ደስ አላቸው፤ የእግዚአብሔርንም ቃል አከበሩ፤ ለዘለዓለም ሕይወትም የተዘጋጁ ሁሉ አመኑ።
ከውኃዉም ከወጡ በኋላ የእግዚአብሔር መንፈስ ፊልጶስን ነጥቆ ወሰደው፤ ጃንደረባዉም ከዚያ ወዲያ አላየውም፤ ደስ እያለውም መንገዱን ሄደ።