ሐዋርያት ሥራ 7:53 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመላእክትም ሥርዐት ኦሪትን ተቀብላችሁ አልጠበቃችሁትም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመላእክት አማካይነት የተሰጣችሁንም ሕግ ተቀበላችሁ እንጂ አልጠበቃችሁትም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በመላእክት አማካይነት ሕግን ተቀብላችሁ ነበር፤ ነገር ግን አልጠበቃችሁትም።” |
ሙሴ ኦሪትን ሰጥቶአችሁ የለምን? ከእናንተ አንዱ ስንኳ ኦሪትን የሚያደርግ የለም፤ እንግዲህ ልትገድሉኝ ለምን ትሻላችሁ?”
በምድረ በዳ በማኅበሩ መካከል የነበረ እርሱ ነው፤ በደብረ ሲና ከአነጋገረው መልአክና፤ ከአባቶቻችንም ጋር ለእኛ ሊሰጠን የሕይወትን ቃል የተቀበለ እርሱ ነው።
ታዲያ ኦሪት ለምን ተሠራች? ኦሪትስ ኀጢአትን ታበዛት ዘንድ፥ ተስፋ ያደረገለት ያ ዘር እስኪመጣ ድረስ፥ በመላእክት በኩል በመካከለኛው እጅ ወረደች።
እንዲህም አለ፦ “እግዚአብሔር ከሲና መጣ፤ በሴይርም ተገለጠልን፤ ከፋራን ተራራ፥ ከቃዴስ አእላፋት ጋር ፈጥኖ መጣ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር በቀኙ ነበሩ።