ሐዋርያት ሥራ 5:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሽከሮቻቸውም መጥተው በወኅኒ ቤት አጡአቸውና ተመልሰው ነገሩአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አገልጋዮቹም ወደ እስር ቤቱ ሄደው በዚያ አላገኟቸውም፤ ተመልሰውም እንዲህ አሏቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌሎዎችም መጥተው በወኅኒው አላገኙአቸውም፤ ተመልሰውም “ወኅኒው በጣም በጥንቃቄ ተዘግቶ ጠባቂዎችም በደጁ ፊት ቆመው አገኘን፤ በከፈትን ጊዜ ግን በውስጡ አንድ ስንኳ አላገኘንም፤” አሉአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዘብ ኀላፊዎቹ ግን ወደ ወህኒ ቤት ሄደው ሐዋርያትን በዚያ አላገኙአቸውም፤ ተመልሰውም መጡና መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌሎዎችም መጥተው በወኅኒው አላገኙአቸውም፤ ተመልሰውም፦ “ወኅኒው በጣም በጥንቃቄ ተዘግቶ ጠባቂዎችም በደጁ ፊት ቆመው አገኘን፥ በከፈትን ጊዜ ግን በውስጡ አንድ ስንኳ አላገኘንም” አሉአቸው። |
“ወኅኒ ቤቱንም ዙሪያውን ተዘግቶ በቍልፍም ተቈልፎ አገኘነው፤ ወታደሮቹም በሩን ይጠብቁ ነበር፤ ነገር ግን ከፍተን በገባን ጊዜ በውስጥ ያገኘነው የለም” አሉአቸው።
ከዚህም በኋላ የቤተ መቅደሱ ሹም ከሎሌዎቹ ጋር ሔዶ አባብሎ አመጣቸው፤ በግድም አይደለም፤ በድንጋይ እንዳይደበድቧቸው ሕዝቡን ይፈሩ ነበርና።