ኪራምም በእነዚያ መርከቦች ከሰሎሞን አገልጋዮች ጋር ባሕሩን መቅዘፍ የሚያውቁ መርከበኞች አገልጋዮቹን ላከ።
ሐዋርያት ሥራ 27:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዐሥራ አራተኛውም ቀን በመንፈቀ ሌሊት በአድርያ ባሕር ስንጓዝ ቀዛፊዎች ወደ የብሱ የደረሱ መሰላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዐሥራ አራተኛው ሌሊት በአድርያ ባሕር ላይ ከወዲያ ወዲህ ስንገላታ፣ እኩለ ሌሊት ገደማ መርከበኞቹ ወደ መሬት የተቃረቡ መሰላቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዐሥራ አራተኛውም ሌሊት በአድርያ ባሕር ወዲህና ወዲያ ስንነዳ፥ መርከበኞች በእኩለ ሌሊት ወደ አንድ ምድር የቀረቡ መሰላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዐሥራ አራተኛው ሌሊት በአድርያ ባሕር መካከል ላይ በነፋስ እየተንገላታን ስንሄድ እኩለ ሌሊት ላይ መርከበኞች ወደ ምድር የቀረቡ መሰላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአሥራ አራተኛውም ሌሊት በአድርያ ባሕር ወዲህና ወዲያ ስንነዳ፥ መርከበኞች በእኩለ ሌሊት ወደ አንድ ምድር የቀረቡ መሰላቸው። |
ኪራምም በእነዚያ መርከቦች ከሰሎሞን አገልጋዮች ጋር ባሕሩን መቅዘፍ የሚያውቁ መርከበኞች አገልጋዮቹን ላከ።
የመርከቡም አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “ምነው ተኝተሃል? እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ያድነን ዘንድ ተነሥተህ አምላክህን ጥራ” አለው።
ከዚህ በኋላም ቀዛፊዎቹ ከመርከብ ሊኮበልሉ በወደዱ ጊዜ ወደ ኋላ ሊመለሱ ከምድር ላይ ሆነው መርከባቸውን የሚያጠናክሩ መስለው ጀልባቸውን ወደ ባሕር አወረዱ።