ሐዋርያት ሥራ 27:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሦስተኛውም ቀን በመርከብ ያለውን ሁሉ በእጃችን እያነሣን በባሕር ላይ ጣልን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሦስተኛውም ቀን፣ የመርከቧን ሸራ ማውጫና ማውረጃ መሣሪያ በገዛ እጃቸው ነቃቅለው ወደ ባሕር ጣሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሦስተኛውም ቀን የመርከቡን ዕቃ በእጃችን ወረወርን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሦስተኛውም ቀን ለመርከቡ የሚያገለግሉትን ዕቃዎች በገዛ እጃቸው እየወረወሩ ጣሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሦስተኛውም ቀን የመርከቡን ዕቃ በእጃችን ወረወርን። |
መርከበኞቹም ፈሩ፤ እያንዳንዱም ወደ አምላኩ ጮኸ፤ መርከቢቱም እንድትቀልልላቸው በውስጥዋ የነበረውን ዕቃ ወደ ባሕር ጣሉት፤ ዮናስ ግን ወደ መርከቡ ውስጠኛው ክፍል ወርዶ ነበር፥ ተኝቶም ያንኳርፍ ነበር።