ሐዋርያት ሥራ 27:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልከኛ የአዜብ ነፋስም ነፈሰ፤ እነርሱም እንደ ወደዱ የሚደርሱ መስሎአቸው ነበር፤ መልሕቁንም አነሡ፤ በቀርጤስም አጠገብ ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መጠነኛ የደቡብ ነፋስ በነፈሰ ጊዜም እንዳሰቡት የሆነላቸው መስሏቸው መልሕቁን ነቅለው፣ የቀርጤስን ዳርቻ በመያዝ ተጓዙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልከኛም የደቡብ ነፋስ በነፈሰ ጊዜ፥ እንዳሰቡት የሆነላቸው መስሎአቸው ተነሡ፤ በቀርጤስም አጠገብ ጥግ ጥጉን አለፉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አነስተኛ የደቡብ ነፋስ ሲነፍስ ባዩ ጊዜ እንዳሰቡት የሆነላቸው መስሎአቸው መልሕቃቸውን አንሥተው ጒዞአቸውን ለመቀጠል ተነሡ፤ ከወደቡም ተነሥተው በቀርጤስ አጠገብ አድርገው ጥግ ጥጉን አለፉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልከኛም የደቡብ ነፋስ በነፈሰ ጊዜ፥ እንዳሰቡት የሆነላቸው መስሎአቸው ተነሡ በቀርጤስም አጠገብ ጥግ ጥጉን አለፉ። |
የሰሜን ነፋስ ሆይ፥ ተነሥ፥ የደቡብም ነፋስ ና፤ በገነቴ ላይ ንፈስ፥ ሽቱዬም ይፍሰስ፤ ልጅ ወንድሜ ወደ ገነቱ ይውረድ፥ መልካሙንም ፍሬ ይብላ።
ከቀርጤስና ከዐረብም የመጣን፥ እነሆ፥ የእግዚአብሔርን ጌትነት በየሀገራችን ቋንቋ ሲናገሩ እንሰማቸዋለን።”
ያም ወደብ ክረምቱን ሊከርሙበት የማይመች ነበር፤ ስለዚህም ብዙዎች ከዚያ ይወጡ ዘንድ ይቻላቸው እንደ ሆነ በቀኝ በኩል ወደ አለው ፊንቄ ወደሚባለው ወደ ሁለተኛው የቀርጤስ ወደብ ይደርሱ ዘንድ ወደዱ።
ከእኛም መብል የበላ አልነበረም። ጳውሎስም ተነሥቶ በመካከል ቆመና እንዲህ አላቸው፥ “እናንተ ሰዎች ሆይ፥ ቀድሞ ቃሌን ሰምታችሁኝ ቢሆን ከቀርጤስም ባትወጡ ኖሮ ከዚህ ጕዳትና መከራ በዳናችሁ ነበር።
ባጠገብዋም በጭንቅ ስናልፍ ላሲያ ለምትባለው ከተማ አቅራቢያ ወደ ሆነችው መልካም ወደብ ወደምትባለው ቦታ ደረስን።