ነገር ግን ካመኑት ከፈሪሳውያን ወገን አንዳንዶች ተነሥተው፥ “ትገዝሩአቸው ዘንድና የሙሴን ሕግ እንዲጠብቁ ታዝዙአቸው ዘንድ ይገባል” አሉ።
ሐዋርያት ሥራ 26:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሊመሰክሩም ከወደዱ እኔ ፈሪሳዊ ሆኜ በአባቶቻችን ሕግ እንደምኖር ከጥንት ጀምሮ እነርሱ ያውቁልኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ስለሚያውቁኝ ከሃይማኖታችን እጅግ ጥብቅ በሆነው ወገን ውስጥ ሆኜ እንደ አንድ ፈሪሳዊ መኖሬን ሊመሰክሩ ፈቃደኞች ከሆኑ ቃላቸውን ሊሰጡ ይችላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሊመሰክሩ ይወዱ እንደሆነ፥ በአምልኮአችን ከሁሉ ይልቅ ሕግን በመጠንቀቅ እንደሚተጋ ወገን ፈሪሳዊ ሆኜ እንደኖርሁ ከጥንት ጀምረው አውቀውኛልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም ሊመሰክሩ ቢፈቅዱ ከሃይማኖታችን በጣም ወግ አጥባቂ ከሆነው ክፍል ፈሪሳዊ ሆኜ እንደ ኖርኩ ከመጀመሪያው አንሥቶ ያውቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሊመሰክሩ ይወዱ እንደ ሆነ፥ በአምልኮአችን ከሁሉ ይልቅ ሕግን በመጠንቀቅ እንደሚተጋ ወገን ፈሪሳዊ ሆኜ እንደኖርሁ ከጥንት ጀምረው አውቀውኛልና። |
ነገር ግን ካመኑት ከፈሪሳውያን ወገን አንዳንዶች ተነሥተው፥ “ትገዝሩአቸው ዘንድና የሙሴን ሕግ እንዲጠብቁ ታዝዙአቸው ዘንድ ይገባል” አሉ።
ጳውሎስም እንዲህ አላቸው፥ “እኔ አይሁዳዊ ሰው ነኝ፤ የቂልቅያ ክፍል በምትሆን በጠርሴስ ከተማ ተወለድሁ፤ በዚችም ከተማ ከገማልያል እግር ሥር ሆኜ አደግሁ፤ የአባቶችንም ሕግ ተማርሁ፤ እናንተ ሁላችሁ ዛሬ እንደምታደርጉትም ለእግዚአብሔር ቀናተኛ ነበርሁ።
እንዲቀጡም ከዚያ ያሉትን አስሬ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣቸው ዘንድ በደማስቆ ወደ አሉ ወንድሞች እንድሄድ ከእነርሱ ዘንድ የሥልጣን ደብዳቤ የተቀበልኋቸው ሊቀ ካህናቱና መምህራን ሁሉ ይመሰክራሉ።
ጳውሎስም እኩሌቶቹ ሰዱቃውያን እኩሌቶቹም ፈሪሳውያን እንደ ሆኑ ዐውቆ፥ “እኔ ፈሪሳዊ የፈሪሳዊ ልጅ ነኝ፤ ስለ ተስፋና ስለ ሙታን መነሣትም ይፈረድብኛል” ብሎ በአደባባይ ጮኸ።
ነገር ግን ይህን አረጋግጥልሃለሁ፤ እኔ በሕግ ያለውን፥ በነቢያትም የተጻፈውን ሁሉ አምኜ እነርሱ ክህደት ብለው በሚጠሩት ትምህርት የአባቶችን አምላክ አመልከዋለሁ።
ይህን ሰው ሲሳደብና ወንጀል ሲሠራ፥ አይሁድንም ሁሉ በየሀገሩ ሲያውክ፥ ናዝራውያን የተባሉት ወገኖች የሚያስተምሩትንም ክህደት ሲያስተምር አግኝተነዋል።