ሐዋርያት ሥራ 25:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጳውሎስ ግን እንቢ ብሎ፥ እንዲድን ወደ ቄሣር ይግባኝ አለ፤ ከዚህም በኋላ ወደ ቄሣር እስክልከው ድረስ እንዲጠብቁት አዘዝሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ጳውሎስ ጕዳዩ በንጉሠ ነገሥቱ እንዲታይለት ይግባኝ ባለ ጊዜ፣ እኔም ወደ ቄሳር እስከምልከው ድረስ እስር ቤት እንዲቈይ አዘዝሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጳውሎስ ግን አውግስጦስ ቄሣር እስኪቆርጥ ድረስ እንዲጠበቅ ይግባኝ ባለ ጊዜ፥ ወደ ቄሣር እስክሰደው ድረስ ይጠበቅ ዘንድ አዘዝሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ግን ጉዳዩ በሮም ንጉሠ ነገሥት እንዲታይለት ፈልጎ ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ይግባኝ በማለቱ ወደ እዚያ እስክልከው ድረስ በእስር ቤት እንዲቈይ አዘዝኩ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጳውሎስ ግን አውግስጦስ ቄሣር እስኪቈርጥ ድረስ እንዲጠበቅ ይግባኝ ባለ ጊዜ፥ ወደ ቄሣር እስክሰደው ድረስ ይጠበቅ ዘንድ አዘዝሁ።” |
አይሁድ ግን ሊቃወሙኝ በተነሡ ጊዜ ወደ ቄሣር ይግባኝ ለማለት ግድ ሆነብኝ፤ ነገር ግን ወገኖችን የምከስበት ነገር ኖሮኝ አይደለም።