እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ “ስለ እርሱ ዛሬ በሕልም እጅግ መከራ ተቀብያለሁና በዚያ ጻድቅ ሰው ምንም አታድርግ፤” ብላ ላከችበት።
ሐዋርያት ሥራ 25:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ፤ በዚሁ በተሰበሰቡ ጊዜ ሳልዘገይ በማለዳ በፍርድ ወንበር ተቀምጬ፥ ያን ሰው እንዲያመጡት አዘዝሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ከሳሾቹ ከእኔ ጋራ ወደዚህ በመጡ ጊዜ፣ ጕዳዩን ሳላጓትት በማግስቱም ችሎት ተቀምጬ ያን ሰው እንዲያቀርቡት አዘዝሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም በዚህ በተሰበሰቡ ጊዜ፥ ሳልዘገይ በማግሥቱ በፍርድ ወንበር ተቀምጬ ያንን ሰው ያመጡት ዘንድ አዘዝሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ከሳሾቹ ተሰብስበው ወደዚህ በመጡ ጊዜ ሳልዘገይ በማግስቱ በፍርድ ወንበር ተቀመጥሁና ጳውሎስን በፊቴ እንዲያቀርቡት አዘዝኩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም በዚህ በተሰበሰቡ ጊዜ፥ ሳልዘገይ በማግሥቱ በፍርድ ወንበር ተቀምጬ ያንን ሰው ያመጡት ዘንድ አዘዝሁ። |
እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ “ስለ እርሱ ዛሬ በሕልም እጅግ መከራ ተቀብያለሁና በዚያ ጻድቅ ሰው ምንም አታድርግ፤” ብላ ላከችበት።
ጳውሎስም መልሶ እንዲህ አለው፤ “እኔ ወደ ቄሣር ዙፋን ችሎት እቀርባለሁ፤ ፍርዴም በዚያ ሊታይልኝ ይገባል፤ በአይሁድም ላይ የበደልሁት በደል እንደሌለኝ ከሰው ሁሉ ይልቅ አንተ ራስህ ታውቃለህ።
ስምንት ወይም ዐሥር ቀን በእነርሱ ዘንድ ከሰነበተ በኋላ ወደ ቂሣርያ ሄደ፤ በማግሥቱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ጳውሎስን እንዲያመጡት አዘዘ።