Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 25:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ስም​ንት ወይም ዐሥር ቀን በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ከሰ​ነ​በተ በኋላ ወደ ቂሣ​ርያ ሄደ፤ በማ​ግ​ሥ​ቱም በፍ​ርድ ወን​በር ተቀ​ምጦ ጳው​ሎ​ስን እን​ዲ​ያ​መ​ጡት አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ከእነርሱም ጋራ ስምንት ወይም ዐሥር ቀን ያህል ከሰነበተ በኋላ፣ ወደ ቂሳርያ ወረደ፤ በማግስቱም ፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ ጳውሎስን እንዲያመጡት አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በእነርሱም ዘንድ ከስምንት ወይም ከዐሥር የማይበልጥ ቀን ተቀምጦ ወደ ቂሳርያ ወረደ፤ በነገውም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ጳውሎስን ያመጡት ዘንድ አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ፊስጦስ ከስምንት ወይም ከዐሥር ቀኖች ያልበለጠ ጊዜ ከእነርሱ ጋር ካሳለፈ በኋላ ወደ ቂሳርያ ሄደ፤ እዚያ በደረሰ ጊዜ በማግስቱ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀመጠና ጳውሎስን እንዲያቀርቡት አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በእነርሱም ዘንድ ከስምንት ወይም ከአስር የማይበልጥ ቀን ተቀምጦ ወደ ቂሳርያ ወረደ፤ በነገውም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ጳውሎስን ያመጡት ዘንድ አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 25:6
11 Referencias Cruzadas  

ከዚ​ህም በኋላ፤ በዚሁ በተ​ሰ​በ​ሰቡ ጊዜ ሳል​ዘ​ገይ በማ​ለዳ በፍ​ርድ ወን​በር ተቀ​ምጬ፥ ያን ሰው እን​ዲ​ያ​መ​ጡት አዘ​ዝሁ።


ጳው​ሎ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፤ “እኔ ወደ ቄሣር ዙፋን ችሎት እቀ​ር​ባ​ለሁ፤ ፍር​ዴም በዚያ ሊታ​ይ​ልኝ ይገ​ባል፤ በአ​ይ​ሁ​ድም ላይ የበ​ደ​ል​ሁት በደል እን​ደ​ሌ​ለኝ ከሰው ሁሉ ይልቅ አንተ ራስህ ታው​ቃ​ለህ።


እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ “ስለ እርሱ ዛሬ በሕልም እጅግ መከራ ተቀብያለሁና በዚያ ጻድቅ ሰው ምንም አታድርግ፤” ብላ ላከችበት።


እናንተ ግን ድኾችን አዋረዳችሁ። ባለ ጠጎቹ የሚያስጨንቁአችሁ አይደሉምን? ወደ ፍርድ ቤትም የሚጎትቱአችሁ እነርሱ አይደሉምን?


መል​ካም ቢሆን፥ ክፉም ቢሆን በሥ​ጋ​ችን እንደ ሠራ​ነው ዋጋ​ች​ንን እን​ቀ​በል ዘንድ፥ ሁላ​ችን በክ​ር​ስ​ቶስ የፍ​ርድ ዙፋን ፊት እን​ቆ​ማ​ለ​ንና።


ጲላ​ጦ​ስም ይህን ሰምቶ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ወደ ውጭ አወ​ጣው፤ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስ​ጥም ገበታ ተብሎ በሚ​ጠ​ራው “ጸፍ​ጸፍ” በሚ​ሉት ቦታ ላይ በወ​ን​በር ተቀ​መጠ።


ፊል​ጶ​ስም አዛ​ጦን ወደ​ም​ት​ባል ሀገር ደረሰ፤ በከ​ተ​ማ​ዎ​ችም ሁሉ እየ​ተ​ዘ​ዋ​ወረ ወደ ቂሳ​ርያ እስ​ኪ​ደ​ርስ ድረስ ያስ​ተ​ምር ነበር።


ፊስ​ጦ​ስም ወደ ቂሣ​ርያ ደርሶ ሦስት ቀን ሰነ​በተ፤ ከዚ​ህም በኋላ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጣ።


ፊስ​ጦ​ስም ጳው​ሎ​ስን በቂ​ሣ​ርያ እን​ደ​ሚ​ጠ​ብ​ቁት፥ እር​ሱም ራሱ ወደ​ዚ​ያው በቶሎ እን​ደ​ሚ​ሄድ መለ​ሰ​ላ​ቸው።


አይ​ሁ​ድ​ንም፥ “ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ የሚ​ችሉ ካሉ ከከ​ሰ​ሳ​ች​ሁት ከዚያ ሰው ጋር እን​ዲ​ከ​ራ​ከሩ ከእኔ ጋር ይው​ረዱ” አላ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios