| ሐዋርያት ሥራ 25:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ጳውሎስም መልሶ እንዲህ አለው፤ “እኔ ወደ ቄሣር ዙፋን ችሎት እቀርባለሁ፤ ፍርዴም በዚያ ሊታይልኝ ይገባል፤ በአይሁድም ላይ የበደልሁት በደል እንደሌለኝ ከሰው ሁሉ ይልቅ አንተ ራስህ ታውቃለህ።Ver Capítulo አዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ጳውሎስም እንዲህ አለ፤ “አሁንም ቢሆን ፍትሕ ማግኘት በምችልበት፣ በቄሳር ፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ፤ አንተ ራስህ በሚገባ እንደምታውቀው በአይሁድ ላይ ምንም በደል አልፈጸምሁም፤Ver Capítulo መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ጳውሎስ ግን “እፋረድበት ዘንድ በሚገባኝ በቄሣር ፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ። አንተው ደግሞ ፈጽመህ እንደምታውቅ አይሁድን ምንም አልበደልኩም።Ver Capítulo አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ጳውሎስ ግን እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፤ “እነሆ! እኔ ልፋረድበት በሚገባኝ በሮም ንጉሠ ነገሥት የፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ፤ አንተም በደንብ እንደምታውቀው በአይሁድ ላይ ያደረግኹት ምንም በደል የለም፤Ver Capítulo መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ጳውሎስ ግን፦ “እፋረድበት ዘንድ በሚገባኝ በቄሳር ፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ። አንተው ደግሞ ፈጽመህ እንደምታውቅ አይሁድን ምንም አልበደልኩም።Ver Capítulo |