ሐዋርያት ሥራ 23:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰዱቃውያን፥ “ሙታን አይነሡም፤ መልአክም የለም፤ መንፈስም የለም” ይላሉና፤ ፈሪሳውያን ግን ይህ ሁሉ እንዳለ ያምናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዱቃውያን የሙታን ትንሣኤ የለም፤ መላእክትም መናፍስትም የሉም የሚሉ ሲሆኑ፣ ፈሪሳውያን ግን በእነዚህ ሁሉ መኖር የሚያምኑ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰዱቃውያን “ትንሣኤም መልአክም መንፈስም የለም፤” የሚሉ ናቸውና፤ ፈሪሳውያን ግን ሁለቱን ያምናሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዱቃውያን “ትንሣኤ የለም፤ መላእክትም የሉም፤ መንፈስም የለም” ሲሉ ፈሪሳውያን ግን “እነዚህ ሁሉ አሉ” ብለው ያምናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዱቃውያን፦ ትንሣኤም መልአክም መንፈስም የለም የሚሉ ናቸውና፤ ፈሪሳውያን ግን ሁለቱን ያምናሉ። |
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶአል ብለን ለሌላው የምናስተምር ከሆነ፥ እንግዲህ ከመካከላችሁ ሙታን አይነሡም የሚሉ እንዴት ይኖራሉ?