Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 23:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ታላቅ ውካ​ታም ሆነ፤ ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ወገን የሆኑ ጸሐ​ፍት ተነ​ሥ​ተው ይጣ​ሉና ይከ​ራ​ከሩ ጀመሩ፤ “በዚህ ሰው ላይ ያገ​ኘ​ነው ክፉ ነገር የለም፤ መን​ፈስ ወይም መል​አክ ተና​ግ​ሮት እንደ ሆነ እንጃ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር አን​ጣላ” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ታላቅ ሁከትም ሆነ፤ ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ አንዳንድ የኦሪት ሕግ መምህራንም ተነሥተው፣ “በዚህ ሰው ላይ ምንም ጥፋት አላገኘንበትም፤ መንፈስ ወይም መልአክ ተናግሮትስ እንደ ሆነ ምን ይታወቃል?” በማለት አጥብቀው ተከራከሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ታላቅ ጩኸትም ሆነ፤ ከፈሪሳውያንም ወገን የሆኑት ጻፎች ተነሥተው “በዚህ ሰው ላይ ምንም ክፉ ነገር አላገኘንበትም፤ መንፈስ ወይስ መልአክ ተናግሮት ይሆን?” ብለው ተከራከሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በዚህ ጊዜ ታላቅ ሁካታ ሆነ፤ ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ አንዳንድ የሕግ መምህራንም ተነሡና “እኛ በዚህ ሰው ላይ ምንም ክፉ ነገር አላገኘንበትም፤ መንፈስ ወይም መልአክ ተናግሮት ይሆናል፤ እኛ ምን እናውቃለን?” በማለት ተከራከሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ታላቅ ጩኸትም ሆነ፥ ከፈሪሳውያንም ወገን የሆኑት ጻፎች ተነሥተው፦ በዚህ ሰው ላይ ምንም ክፉ ነገር አላገኘንበትም፤ መንፈስ ወይስ መልአክ ተናግሮት ይሆን? ብለው ተከራከሩ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 23:9
23 Referencias Cruzadas  

በም​ድር ላይም ወደ​ቅሁ ‘ሳውል ሳውል ለምን ታሳ​ድ​ደ​ኛ​ለህ?’ የሚል ቃል​ንም ሰማሁ።


በዚያ ቆመው ይሰሙ የነ​በሩ ሕዝብ ግን “ነጐ​ድ​ጓድ ነው” አሉ፤ “መል​አክ ተና​ገ​ረው” ያሉም አሉ።


ለብ​ቻ​ቸ​ውም ገለል ብለው እርስ በር​ሳ​ቸው እን​ዲህ ብለው ተነ​ጋ​ገሩ፥ “ይህ ሰው እን​ዲ​ሞት ወይም እን​ዲ​ታ​ሰር የሚ​ያ​በቃ የሠ​ራው በደል የለም።”


እኔ ግን ለሞት የሚ​ያ​ደ​ር​ሰው በደል እን​ዳ​ል​ሠራ እጅግ መር​ምሬ፥ እር​ሱም ራሱ ወደ ቄሣር ይግ​ባኝ ማለ​ትን ስለ​ወ​ደደ እን​ግ​ዲህ ልል​ከው ቈር​ጫ​ለሁ።


ስለ ሕጋ​ቸ​ውም ብቻ እንደ ከሰ​ሱት ተረ​ዳሁ፤ ለሞ​ትና ለመ​ታ​ሰር የሚ​ያ​በቃ ሌላ በደል ግን የለ​በ​ትም።


ጻፎችና ፈሪሳውያንም ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር ሲበላ አይተው ለደቀ መዛሙርቱ “ከቀራ ጮችና ከኀጢአተኞች ጋር የሚበላና የሚጠጣ ስለ ምንድር ነው?” አሉ።


ቅንነትን የሚሹ ሰላምን ያገኛሉ።


እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​ስ​ቀ​ና​ውን? በውኑ እኛ ከእ​ርሱ እን​በ​ረ​ታ​ለን?


እኔ ለእ​ርሱ የም​ሆ​ንና የማ​መ​ል​ከው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የላ​ከው መል​አክ በዚች ሌሊት በአ​ጠ​ገቤ ቆሞ ነበ​ርና።


ሰዱ​ቃ​ው​ያን፥ “ሙታን አይ​ነ​ሡም፤ መል​አ​ክም የለም፤ መን​ፈ​ስም የለም” ይላ​ሉና፤ ፈሪ​ሳ​ው​ያን ግን ይህ ሁሉ እን​ዳለ ያም​ናሉ።


እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ለአ​መ​ን​ነው ለእኛ እንደ ሰጠን፥ ያን ጸጋ​ውን እንደ እኛ አስ​ተ​ካ​ክሎ ከሰ​ጣ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልከ​ለ​ክል የም​ችል እኔ ማነኝ?”


በም​ድር ላይም ወደቀ፤ ወዲ​ያ​ውም፥ “ሳውል፥ ሳውል፥ ለምን ታሳ​ድ​ደ​ኛ​ለህ?” የሚ​ለ​ውን ቃል ሰማ።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመጣ ከሆነ ግን ልታ​ፈ​ር​ሱት አት​ች​ሉም፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጋር እን​ደ​ሚ​ጣላ አት​ሁኑ።”


ጲላ​ጦ​ስም ለሦ​ስ​ተኛ ጊዜ፥ “ምን ክፉ ነገር አደ​ረገ? እነሆ፥ ለሞት የሚ​ያ​በቃ ምክ​ን​ያት አላ​ገ​ኘ​ሁ​በ​ትም፤ እን​ኪ​ያስ ልግ​ረ​ፈ​ውና ልተ​ወው” አላ​ቸው።


ጲላ​ጦ​ስም ለካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ለሕ​ዝቡ፥ “በዚህ ሰው ላይ ያገ​ኘ​ሁት አን​ድስ እንኳ በደል የለም” አላ​ቸው።


ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም፥ “ከቀ​ራ​ጮ​ችና ከኃ​ጥ​ኣን ጋር ለምን ትበ​ላ​ላ​ችሁ? ትጠ​ጡ​ማ​ላ​ችሁ?” ብለው በደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ላይ አን​ጐ​ራ​ጐሩ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊት ይህን ቃል ለሳ​ኦል መን​ገር በፈ​ጸመ ጊዜ፥ ሳኦል፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! ይህ ድም​ፅህ ነውን?” አለ፤ ሳኦ​ልም ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ አለ​ቀሰ።


ሳሙ​ኤ​ልም፥ “በእጄ ምንም እን​ዳ​ላ​ገ​ኛ​ችሁ ዛሬ በዚ​ህች ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክር ነው፤ እርሱ የቀ​ባ​ውም ምስ​ክር ነው” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “አዎ ምስ​ክር ነው” አሉ።


አለ​ቆ​ቹና ሕዝ​ቡም ሁሉ ለካ​ህ​ና​ትና ለነ​ቢ​ያተ ሐሰት፥ “ይህ ሰው በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ተና​ግ​ሮ​ና​ልና ሞት አይ​ገ​ባ​ውም” አሉ።


“ከዚህ በኋላ ወደ ደማ​ስቆ ስሄድ ቀትር በሆነ ጊዜ ወደ ከተ​ማው አቅ​ራ​ቢያ ደርሼ ሳለሁ ድን​ገት ታላቅ መብ​ረቅ ከሰ​ማይ በእኔ ላይ አን​ፀ​ባ​ረቀ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios