የአባቶቻችሁም ሥራ ደስ አሰኝቶአችኋል፤ የምትመሰክሩባቸውም እናንተ ራሳችሁ ናችሁ፤ እነርሱ የገደሉአቸውን መቃብራቸውን እናንተ ትሠራላችሁና።
ሐዋርያት ሥራ 22:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰማዕትህን እስጢፋኖስን በገደሉትም ጊዜ እኔ እዚያ አብሬአቸው ነበርሁ፤ የገዳዮችንም ልብስ እጠብቅ ነበር።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም የአንተን ሰማዕት የእስጢፋኖስን ደም በሚያፈስሱበት ጊዜ፣ በድርጊታቸው ተስማምቼ በቦታው ቆሜ የገዳዮቹን ልብስ እጠብቅ ነበር።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰማዕትህንም የእስጢፋኖስን ደም ባፈሰሱ ጊዜ፥ ራሴ ደግሞ በአጠገባቸው ስቆም ተስማምቼ የገዳዮችን ልብስ እጠብቅ ነበር፤’ አልሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአንተ ምስክር የነበረው እስጢፋኖስ በተገደለ ጊዜ እኔም ራሴ በገዳዮቹ አጠገብ ቆሜ ከእነርሱ ጋር በነገሩ ተስማምቼ ነበር፤ ልብሳቸውንም እጠብቅ ነበር፤’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰማዕትህንም የእስጢፋኖስን ደም ባፈሰሱ ጊዜ፥ ራሴ ደግሞ በአጠገባቸው ስቆም ተስማምቼ የገዳዮችን ልብስ እጠብቅ ነበር አልሁ። |
የአባቶቻችሁም ሥራ ደስ አሰኝቶአችኋል፤ የምትመሰክሩባቸውም እናንተ ራሳችሁ ናችሁ፤ እነርሱ የገደሉአቸውን መቃብራቸውን እናንተ ትሠራላችሁና።
ይህንም በኢየሩሳሌም አደረግሁት፤ ከሊቃነ ካህናትም ሥልጣን ተቀብዬ ከቅዱሳን ብዙዎችን ወደ ወኅኒ ቤት አስገባኋቸው፤ ሲገድሏቸውም አብሬ እመክር ነበርሁ።
ይህም ነገር በእነርሱ ዘንድ የተወደደ ሆነ፤ ሃይማኖቱ የቀናና መንፈስ ቅዱስ ያደረበትን ሰው እስጢፋኖስን፥ ፊልጶስን፥ ጵሮኮሮስን፥ ኒቃሮናን፥ ጢሞናን፥ ጰርሜናን፥ ወደ ይሁዲነት የተመለሰውን የአንጾኪያውን ኒቆላዎስንም መረጡ።
ከከተማም ወደ ውጭ ጐትተው አውጥተው ወገሩት፤ የሚወግሩት ሰዎችም ልብሳቸውን ሳውል በሚባል ጐልማሳ እግር አጠገብ አስቀመጡ።
በዚያ ወራትም በኢየሩሳሌም ባለችው ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ሆነ፤ ከሐዋርያትም በቀር ሁሉም በይሁዳና በሰማርያ ባሉ አውራጃዎች ሁሉ ተበተኑ።
ይህን እንዲህ ላደረገ ሞት እንደሚገባው እነርሱ ራሳቸው የእግዚአብሔርን ፍርድ እያወቁ፥ እነርሱ ብቻ የሚያደርጉት አይደለም፤ ነገር ግን ሌላውን ያነሣሡታል፤ ያሠሩታልም።
“የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፤ ሰይጣንም በሚኖርበት፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ ሃይማኖቴን አልካድህም።