ሐዋርያት ሥራ 22:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ‘ስለ እኔ የምትመሰክረውን ምስክርነት አይቀበሉህምና ከኢየሩሳሌም ፈጥነህ ውጣ’ ሲለኝ አየሁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታም ሲናገረኝ አየሁ፤ እርሱም አሁኑኑ፣ ‘ፈጥነህ ከኢየሩሳሌም ውጣ! ስለ እኔ የምትመሰክረውን አይቀበሉህምና’ አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ‘ፍጠን፤ ከኢየሩሳሌምም ቶሎ ውጣ፤ ስለ እኔ የምትመሰክረውን አይቀበሉህምና፤’ ሲለኝ አየሁት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታም ተገልጦልኝ ‘አንተ ስለ እኔ የምትሰጠውን ምስክርነት ስለማይቀበሉ ሳትዘገይ በፍጥነት ከኢየሩሳሌም ውጣ’ አለኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ፍጠን ከኢየሩሳሌምም ቶሎ ውጣ፥ ስለ እኔ የምትመሰክረውን አይቀበሉህምና ሲለኝ አየሁት። |
በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፤ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም።
ያንጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራራ ይሽሹ፤ በመካከልዋ ያሉም ከእርስዋ ይውጡ፤ በአውራጃዎችዋ ያሉም ወደ እርስዋ አይግቡ።
እኔ ነጻ አይደለሁምን? ሐዋርያስ አይደለሁምን? ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ያየሁ አይደለሁምን? እናንተስ በጌታችን ሥራዬ አይደላችሁምን?