ሐዋርያት ሥራ 20:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተሰብስበን በነበርንበት ሰገነትም ብዙ መብራት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተሰበሰብንበትም ሰገነት ላይ ብዙ መብራት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተሰብስበንም በነበርንበት ሰገነት እጅግ መብራት ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ በተሰበሰብንበት ፎቅ ብዙ መብራት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተሰብስበንም በነበርንበት ሰገነት እጅግ መብራት ነበረ። |
ወደ ማደሪያቸውም በደረሱ ጊዜ ጴጥሮስ፥ ዮሐንስ፥ ያዕቆብ፥ እንድርያስ፥ ፊልጶስ፥ ቶማስ፥ ማቴዎስ፥ በርተሎሜዎስ፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፥ ቀናተኛው ስምዖን፥ የያዕቆብ ልጅ ይሁዳም ወደሚኖሩበት ሰገነት ወጡ።
ስሙ አውጤክስ የሚባል አንድ ጐልማሳ ልጅም በመስኮት በኩል ተቀምጦ ሳለ ከባድ እንቅልፍ አንቀላፍቶ ነበር፤ ጳውሎስም ትምህርቱን ባስረዘመ ጊዜ ያ ጐልማሳ ከእንቅልፉ ብዛት የተነሣ ከተኛበት ከሦስተኛው ፎቅ ወደ ታች ወደቀ፤ ሬሳውንም አነሡት።